የዶክተር ያየህይራድ ቅጣው የግለ-ታሪክ መፅሐፍ ተመረቀ

Date:

“ከእናት እቅፍ እስከ ልጅ ልጅ ምርኲዝ ትዝታዎቼ ” የሚል ርዕስ የተሰጠው  የዶክተር ያየህይራድ መፅሐፍ ቅዳሜ ጥር 9 2018 ዓ ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ መኮንን አዳራሽ ተመርቋል። በምረቃውም ላይ የቀድሞ የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ክብርት ወይዘሮ ሣህለወርቅ ዘውዴ ለባለታሪኩ ክብር ሲሉ የቪድዮ መልዕክት ልከው እንዲደመጥ አድርገዋል።

    አማዞን ላይ ጭምር በመሸጥ ላይ የሚገኘው ይህ መፅሐፍ 350 ገፆች አሉት፡፡ የመፅሐፍ ዝግጅቱን እና ምረቃውን ያከናወነው ተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን ( ዕዝራ እጅጉ) ሲሆን አርትኦቱም በናይእግዚ ኅሩይ ተሠርቷል።

መፅሀፉ በተመረቀበት ዕለት ‘ታላላቆችን እናክብር’ የተሰኘውን የተወዳጅ ሚድያ ሽልማት ዶክተር ያየህይራድ እንዲያገኙ ተደርጓል። ከዚህ ቀደም በህይወት ያሉና የሌሉትን ጨምሮ ከ21 በላይ ባለውለታ ኢትዮጵያዊያንን ተወዳጅ ሚድያ ዕውቅና መስጠቱ አይዘነጋም።

በዕለቱ፣ በዶክተር ያየህይራድ ቅጣው ላይ ያተኮረ  የ3 ሰዓት የድምፅ ዶክመንተሪ በይፋ የተመረቀ ሲሆን ሳቤህ ዞንና ተወዳጅ ሚድያ በትብብር ያሰናዱት ነው።ይህ የድምፅ ዘጋቢ ሥራ በ tewedajemedia tube ላይ የተጫነ ስለመሆኑም ተነግሯል።

ዶክተር ያየህይራድ ቅጣው፣ ከጄነራል ዊንጌት ትምህርትቤት ብርቱ ተማሪዎች አንዱ የነበሩ ሲሆን በፈረንሳይ አገርም የህክምና ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው፡፡

የዕድገት በሕብረት ዘመቻ ላይ የማይዘነጋ አሻራ ያኖሩት ዶክተር ያየህይራድ ቅጣው፣በትምህርት ሚኒስትርነት እናት አገራቸውን በትጋት ያገለገሉ ናቸው፡፡

የመፅሐፉን የአርትዖት ሥራ 5 ወር የወሰደ ሲሆን አጠቃላይ የመፅሀፉ ፕሮጀክት 8 ወራትን መውሰዱን የስነዳ ሥራው አስተባባሪ  ዕዝራ እጅጉ ተናግሯል። የምረቃ መርሀ- ግብሩ  ላይ ታላላቅ እንግዶች የታደሙ ሲሆን  ደመላሽ አማረ መፅሀፉን እንድናነብ የሚጋብዝ አጠር ያለ ዳሰሳ አቅርቧል።

  የዶክተር ያየህይራድ ቅጣው ወዳጅ የሆኑት ፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላ ከወጣትነት አንስቶ ከባለታሪኩ ጋር የነበራቸውን ትዝታና የአብሮአደግ ቀረቤታ እምን ድረስ እንደሆነ ተርከዋል።

ሳምራዊት አዘነ እና ዕንቁ ዜማዎች የባለታሪኩ ሙያ እና የህይወት ተሞክሮ የመጠነ የሙዚቃ ሥራ አቅርበዋል።

የባለታሪኩ የዶክተር ያየህይራድ ቅጣው ባለቤትና ልጆችም ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። ሁሉም በአንድ ድምፅ ኢትዮጵያ እንደዚህ አይነት ሰው በማፍራቷ ኩራት ይሰማናል ብለዋል።

በመርሀ- ግብሩ ላይ በርካታ ባለውለታ  ኢትዮጵያውያን የታደሙ  ሲሆን  ከእነዚህም ውስጥ  ዶክተር ኃይሉ አርአያ፣ ወይዘሮ መአዛ ቅጣው፣ፕሮፌሰር ሺፈራው በቀለ፣ወይዘሮ ሩት አማኑኤል አብርሃም፣ዶክተር አዜብ ታምራት ፣ጀነራል አዲስ ተድላ ፣ጀነራል ካሣዬ ጨመዳ፣ እና ሌሎችም ይገኙበታል ።

የዚህ መፅሀፍ የአርትዖት አስተባባሪ  እና ሁነት አዘጋጅ፣ ዕዝራ እጅጉ 21 መፅሀፍትን እስከዛሬ ሠርቶ ያስነበበ ሲሆን የ45 ሰዎችንም ታሪክ በሲዲ አሳትሟል። በተጨማሪም የአማርኛ ኢንሳይክሎፒዲያንም አሳትሟል። ወደ 40 የሚጠጉ ሁነቶችንም በተሳካ ሁኔታ እንዲካሄዱ ያደረገ ስለመሆኑም ይታወቃል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አቶ ዳውድ ኢብሳ ከምርጫው ራሳቸውን አገለሉ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ በኦሮሚያ...

ኢራን ከአሜሪካ ጋር ‹‹ሁሉን አቀፍ ስምምነት›› እንደምትፈልግ ገለጸች

ኢራን በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ጦርነት ለማቆም ከአሜሪካ ጋር በምታደርገው...

የሪል እስቴት ዘርፍ ዘመናዊ የክፍያ ቴክኖሎጂን ለማስፋፋት አዲስ አጋርነት ፈጠረ

በኢትዮጵያ የሪል እስቴት ዘርፍ ግንባር ቀደም ከሆኑት ድርጅቶች አንዱ...

የአርቲስት ጥላሁን ገሠሠ መታሰቢያ ሐውልት ተመረቀ

ለኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ዕድገት ወደር የሌለው አስተዋጽኦ ላበረከተውና የሙዚቃው...