የግብጽ እና የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በስልክ ተወያዩ

Date:

የግብጽ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደላቲ እና የኤርትራው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳለህ በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ ሁኔታ እና በቀይ ባህር ዙሪያ በስልክ መምከራቸው ተገለጸ።

የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደላቲ እና የኤርትራ አቻቸው ኦስማን ሳሌህ በሀገራቱ መካከል በሁለትዮሽ ግንኙነት እና በፖለቲካዊ ምክክር የተገኘውን ተጨባጭ እድገት ሲሉ የገለጹትን ለማሳደግ ተወያይተዋል ሲል አህራም ጋዜጣ በዘገባው አስታውቋል፤ በተለያዩ ዘርፎች ያለውን ትብብር ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል ብሏል።

ዘገባው በተጨማሪም ሁለቱ ሚኒስትሮች የሀገራቱን ትብብር እና ትስስረ ለማጠናከር የተወያዩት የግብፁ ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ ኤል ሲሲ እና የኤርትራ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፍወርቂ ያስቀመጡትን መመሪያ ተከትሎ ነው ሲል ጠቁሟል።

ሁለቱም ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በስልክ ባደረጉት ምክክራቸው የሁለቱን ሀገራት ተጠቃሚ በሚያደረጉ በተለያዩ የቀጠናው ጉዳዮች መክረዋል ያለው ዘገባው በተለይም ደግሞ በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ ሁኔታ እና በቀይ ባህረ ዙሪያ መወያየታቸውን አስታውቋል።

ሁለቱም ሚኒስትሮች የቀጠናውን ደህንነት እና መረጋጋት ለማሳደግ በጋራ፣ በቅንጅት የሚያካሂዱትን ትብብር መቀጠል አስፈላጊ መሆኑን አረጋግጠዋል ብሏል።

የግብጹ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርትራ ለመልማት የምታደርገው ጥረት ሀገራቸው እንደምትደግፍ አስታውቀዋል ያለው ዘገባው በተለይም የልማት ፕሮጀክቶቿን እና መረጋጋትን ለማስጠበቅ የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ ግብፅ ያላትን ቁርጠኝነት አፅንዖት ሰጥተዋል ገልጸዋል ብሏል።

በተመሳሳይ የግብፅ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ ኤል ሲሲ #የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድን በግብፅ የባህር ጠረፍ ከተማ ኤል አላሜይን ሰኔ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ተቀብለው ባነጋገሩበት በድጋሚ በቀይ ባህር ደህንነት ላይ ያተኮረ መልዕክት ማስተላለፋቸውን የተመለከተ ዘገባ ማቅረባችን ይታወሳል።

የቀይ ባህርን ደህንነት ለማስጠበቅ እንደሚሰሩ በመግለጽ ግብጽ ለሶማሊያ የምታደርገውን ወታደራዊ ድጋፍ አጠናክራ ትቀጥላለች ማለታቸውም በዘገባው ተካቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች  565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አላሳለፉም

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት...

የአማርኛ ቋንቋ እውነተኛ ምንጭ ቤተ መንግሥት ሳይሆን ሕዝብና ሠራዊት ነው

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም አዘጋጅነት ከስድስት...

አዲስ አበባ፦ የዜጎች ቀይ መስመር!

(የግል አስተያየት) አዲስ አበባ የኢትዮጵያውያን መናገሻ፣ የበርካታ ብሔረሰቦች ባህሎች ለዘመናት...

አብን የምክክሩን ውጤት ውድቅ አደረገ!

አብን በሀገራዊ ምክክሩ ማጠቃለያ ላይ የተፈጸመውን “ሕገ-ወጥ ጣልቃ-ገብነት” በመቃወም...