የፌዴሬሽን ምክር ቤት በአምስት የምርጫ ክልሎች ላይ ውሳኔ አሳለፈ

Date:

የኢትዮጵያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት በአማራ እና በትግራይ ክልላዊ መንግሥታት መካከል የይገባኛል ውዝግብ ባለባቸው አምስት የምርጫ ክልሎች ላይ ልዩ ውሳኔ ማሳለፉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

ምክር ቤቱ ለምርጫ ቦርድ በላከው ደብዳቤ መሠረት፣ በሁለቱ ክልሎች መካከል አከራካሪ ሆነው የቆዩት የሚከተሉት አምስት የምርጫ ክልሎች የይገባኛል ጥያቄያቸው በሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓት እልባት እስከሚያገኝ ድረስ፦

👉ሁመራ
👉አዲረመፅ
👉ኮረም አፍላ
👉ጠለምት
👉ራያ አላማጣ

እነዚህ የምርጫ ክልሎች ከትግራይ ክልላዊ መንግሥት ውጪ ሆነው፣ ለብቻቸው በቀጥታ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ለፌዴራል ፓርላማ) ብቻ ምርጫ እንዲያካሂዱ ተወስኗል።

በሌላ በኩል፣ በእነዚህ አካባቢዎች የሚካሄደው የክልል ምክር ቤት ምርጫ ግን በአሁኑ ወቅት የማይካሄድ መሆኑ ታውቋል። የክልል ምክር ቤት ምርጫው የሚካሄደው በአካባቢዎቹ ላይ የተነሳው የይገባኛል ውዝግብ በሕገ-መንግሥታዊ ውሳኔ እልባት አግኝቶ አመቺ ጊዜ ሲመረጥ ወደፊት እንደሚከናወን ምክር ቤቱ አሳስቧል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በበኩሉ፣ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት የተላለፈለትን ይህንን ውሳኔ መሠረት በማድረግ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አስፈላጊውን የሕግና የሥርዓት ዝግጅት በማድረግ ተግባራዊ እንደሚያደርግ ገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

“ንባብ ለህይወት!” ታላቅ የንባብ ሳምንት እና የመጻሕፍት አውደ ርዕይ

የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት እና የንባብ ለህይወት...

በኢትዮጵያ ከ10 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ ጋር ይኖራሉ

በኢትዮጵያ ከ10 ሚልዮን በላይ ሰዎች ከሄፓታይተስ ቢ እና ከ2...

የቶዮታ ኮሮላ መኪና በኤሌክትሪክ ሊመጣ ነዉ

የዓለማችን ግዙፍ የመኪና አምራች የሆነው ቶዮታ፤ እንደ ቴስላ እና...

ኢራንን ለመምታት የዩናይትድ ስቴትስ ጄቶች ከምድሯ ይነሱ እንደነበር እሥራኤል ይፋ አደረገች

የእሥራኤል መከላከያ ሚንሥትር እሥራኤል ካትስ የዩናይትድ ስቴትስ የጦር ጄቶች...