ያልተመጣጠነው የደሞዝ ልዩነት

Date:

በአለም አቀፍ ደረጃ የድርጅቶች ዋና ስራ አስፈፃሚዎች ከ2019 ወዲህ ክፍያቸው በ50 በመቶ ሲጨምር የመደበኛ ሰራተኞች ክፍያ ግን የጨመረው በ0.9% ብቻ ነው።

አማካይ የድርጅቶች ዋና ስራ አስፈፃሚዎች ክፍያ በ2019 ከነበረበት 2.9 ሚሊየን ዶላር በ2024 4.3 ሚሊየን ዶላር ደርሷል።

አየርላንድ እና ጀርመን ለዋና ስራ አስፈፃሚዎች ከፍተኛ አማካይ ክፍያ የሚከፈልባቸው ሃገራት ሲሆኑ በ2024 በአማካይ በቅደም ተከተል 6.7 ሚሊየን ዶላርና 4.7 ሚሊየን ዶላር አመታዊ ክፍያ ይከፈላል።

በደቡብ አፍሪካ ይህ አማካይ የዋና ስራ አስፈፃሚዎች ክፍያ 1.6 ሚሊየን ዶላር ይደርሳል።

በየጊዜው በድርጅት ዋና ስራ አስፈፃሚዎች እና በመደበኛ ሰራተኞች መካከል ያለው የደመወዘ እድገትና ክፍያ እየሰፋ የመጣ ሲሆን እንደ ኦክስፋም ያሉ ድርጅቶች በነዚህ ሃብታሞች ላይ የሚጣለው ታክስ እንዲጨምር ጥሪ እያደረጉ ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ደቡብ ሱዳን የነዳጅ ቅድመ-ክፍያ ውሎችን እንዳትፈጽም አገደ

የለንደን ፍርድ ቤት ደቡብ ሱዳን ከአሁን በኋላ አዳዲስ የነዳጅ...

” ከ140 በላይ ጠጠር አምራች ድርጅቶች ሙሉ በሙሉ ቆመዋል ” – ማህበሩ

" ካላቸው ቅሬታ ማቅረብ ይችላሉ። ግን መሬቱ መቼ እንደተወሰደባቸው...

ትራምፕ “በኢራን ላይ ሊፈጸም ታቅዶ የነበረውን ጥቃት አንፈጽምም” አሉ

ትራምፕ በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ ቁልፍ የአሜሪካ አጋር ሀገራት መሪዎች...

በነዳጅ ጭማሪ በኬንያ በተቀሰቀሰ ተቃውሞ የአራት ሰዎች ሕይወት አለፈ

በኬንያ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪን ተከትሎ በዋና ከተማዋ ናይሮቢ በጸጥታ...