ጊፍት ሪል ስቴት 2000 ቤቶችን መሸጡን ተናገረ

Date:

በታማኝነቱና በቀልጣፋነቱ በብዙዎች ዘንድ እየተወደደ የመጣው ጊፍት ሪል እስቴት የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ “መኖር በጊፍት መንደር!” በሚል መሪ ቃል ታህሳስ 15 እስከ ታህሳስ 28/2018 ድረስ የሚቆይ የጊፍት ሪል እስቴት የመኖሪያ አፓርትማዎች እና የንግድ ሱቆች የሽያጭ ኤክስፖ የመክፈቻ ስነስርዓት በዜሬው ዕለት በለገሀር የጊፍት መንደር በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና ደንበኞቹ በተገኙበት አካሄደ።

የጊፍት ሪል እስቴት የ2018 ዓ.ም የገና በዓል ኤክስፖ ሽያጭ እስካሁን ባለፉት ስምንት ወራት በተከታታይ ለሰባት ጊዜአት ካደረጋቸው ኤክስፖዎች ልዩ የሚያደርገው፣ በተሻለ አማራጭ፣ በተሻለ ዋጋ፣ በ2% ቅድመ ክፍያ እስከ 20% ቅናሽ ብቻ የመኖሪያና የንግድ ቤት ባለቤት የማድረግ አጋጣሚን ለሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ጊፍት ሪል እስቴት መፍጠሩ መሆኑ ተገልጧል።

የጊፍት ሪልስቴት የኮሚኒኬሽን ሀላፊ የሆኑት ዶ/ር ሰለሞን አሊ የፈረንጆችን ክሪስማስ እና አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ፣ እንዲሁም የኢትዮጵያን ገና በዓል ለማክበር ወደ ውድ እናት አገራችሁ የመጣችሁ እና በመምጣት ላይ የምትገኙ ውድ የውጭ እና የአገር ውስጥ አዳዲስ የጊፍት ደንበኞቻችን፣ ይህንን መልካም አጋጣሚ እንድትጠቀሙ ጊፍት ሪልስቴት ጥሪ ያቀርባል። ብለዋል።

ለዘንድሮው የገና በዓል ኤክስፖ የቀረቡት የጊፍት ሪል እስቴት ዘመናዊ መንደሮች የሚገኙት በመሃል አዲስ አበባ በለገሃር፣ በተ/ሃይማኖት፣ በአትላስ፣ በአፍሪካ የንግድ እና የኮንቨንሽን ማእከል አጠገብ (ሲኤምሲና) በፈረስ ቤት (ደራርቱ ቱሉ አደባባይ) አጠገብ በሚገኙ ሲሆን በዘመናዊ ዲዛይኖች፣በግሪን ሌጋሲ፣ በበቂ የማሕራዊ፣ የጤና፣ የገበያ፣ የመዝናኛ እና ልዩ ልዩ የሜትሮፖሊታን ድባብን ያካተቱ ለአዲሱ ትውልድ እና ለቤተሰቦቻቸው መልካም ስፍራዎች ናቸው ተብሏል።

እስካሁን በተፈጠሩ ተከታታይ ኤክስፖዎች ከ2 ሺህ በላይ ቤቶች መሸጣቸው በመድረኩ ተጠቁሟል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...