ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኳታር ዶሃ ገቡ

Date:

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ፣ የቀድሞው የኳታር አሚር ሼይኽ ሀማድ ቢን ካሊፋ አልታኒ ሕልፈትን ተከትሎ የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ለመግለጽና ለቅሶ ለመድረስ ኳታር ዶሃ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በስፍራው በመገኘት፣ ለኳታር ሕዝብና መንግሥት እንዲሁም ለንጉሣዊው ቤተሰብ የአጋርነትና የጽናት መግለጫ መልእክታቸውን ያደርሳሉ።

ሼይኽ ሀማድ ቢን ካሊፋ አልታኒ ኳታርን ወደ ዘመናዊ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ምዕራፍ ያሸጋገሩ ታላቅ መሪ እንደነበሩ ይታወሳል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዑክ በዶሃ ቆይታው፣ ከሀገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር በኢትዮጵያ እና በኳታር የሁለትዮሽ ግንኙነቶች ዙሪያ አጫጭር ውይይቶችን ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ኔታንያሁ እና ትራምፕ የፊታችን ማክሰኞ በዋይት ሀውስ እንደሚወያዩ ተገለጸ

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት፤ ቤንያሚን ኔታንያሁ ከፕሬዝዳንት ዶናልድ...

አሜሪካ በኢትዮጵያ ያላትን የንግድና ኢንቨስትመንት ትብብር ለማጠናከር ከኢትዮጵያ መንግሥትና ከግሉ ዘርፍ ጋር ውይይት አካሄደች

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ጄ. ማሲንጋ፣ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን...

የካፍ ፕሬዝዳንት የ2027 አፍሪካ ዋንጫ በ24 ተሳታፊ ሀገራት እንደሚካሄድ አስታወቁ

የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን (ካፍ) ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሙትሰፔ የ2027...

የቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ነፃ የጤና ምርመራና ሕክምና መስጠት ጀመረ

ሆስፒታሉ በቀን ከ300 በላይ ታካሚዎችን ያስተናግዳል የቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ከሐምሌ...