ህወሓት “የአፍሪካ ህብረት ፓኔል በአፋጣኘ ተሰብስቦ በፕሪቶርያ የሰላም ስምምነት አተገባበር” ዙሪያ እንዲመክር ጥሪ አቀረበ

Date:

“የፕሪቶርያ የሰላም ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ያሉ ሁኔታዎች አሳሳቢ በመሆናቸው የአፍሪካ ህብረት ፓኔል ውይይት ሊያደርግ ይገባል ሲሉ” የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ሊቀመንበር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ጥሪ አቀረቡ።
ሊቀመንበሩ ይህንን ጥሪ ያቀረቡት በአፍሪካ ህብረት የፕሪቶርያ ስምምነት የክትትል፣ ማረጋገጥ እና ማስከበር ተልዕኮ ኮሚቴ ሃላፊ ሁነው ከተሾሙት ሜጀር ጀነራል ሳማድ አላዴ ትላንት ሚያዚያ 6 ቀነ 2017 ዓ.ም በጽ/ቤታቸው ተቀብለው ባካሄዱት ውይይት መሆኑን ፓርቲው ባጋራው መረጃ አስታውቋል።
“በፕሪቶሪያ ስምምነት መሰረት ከመከላከያ ሰራዊት ውጭ ውጭ ያሉት ታጣቂዎች ከትግራይ ግዛት እስካሁን አለመውጣታቸውን፣ የተሰደዱ እና የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀያቸው መመለስ አለመቻላቸውን እንዲሁም የትግራይ ሉዓላዊ መሬቶች በወራሪዎች ቁጥጥር ስር ይገኛሉ ሲሉ ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ለተሿሚው መናገራቸውንም አካቷል።
ሊቀመንበሩ ደብረጺዮን “የፖለቲካ ድርድር እስካሁን አለመጀመሩን፣ የስምምነቱ ፈራሚ የሆነው ህወሓት የተሰረዘው ህጋዊ ሰውነቱ አለመመለሱን” ለተሿሚው ማስታወቃቸውን መረጃው አመላክቷል።
ሜጀር ጀነራል ሳማድ አላዴ ከዚህ በፊት የህብረቱ ተልዕኮ ኮሚቴ ሃላፊ የነበሩትን ሜጀር ጀነራል ስቴፈን ራዲናን በመተካት የተሾሙ መሆናቸው ተጠቁሟል።
የህብረቱ የስምምነቱ የክትትል፣ ማረጋገጥ እና ማስከበር ተልዕኮ ኮሚቴ “መሬት ላይ ያለውን እውነታ በግልፅ በመለየት ሪፖርቱን እንዲያቀርብ ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ለተሿሚው ማሳሰባቸውን ጽ/ቤታቸው ባጋራው መረጃ አስታውቋል።
የለጋሽ ድርጅቶች የሚያቀርቡት እርዳታ መቋረጥን ተከትሎ ከቀያቸው ተፈናቅለው እና ተሰደው የሚገኙ ነዋሪዎች ለከፋ አደጋ መጋለጣቸውን በመግለጽ በስምምነቱ መሰረት ዋስትናቸው ተረጋግጦ በአፋጣኝ ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ የሚጠበቅባችሁን ልትወጡ ይገባል ሲሉ ለተሿሚው ማሳሰባቸውንም አመላክቷል።
“በወራሪዎች ስር የሚገኘው ህዝባችን ይሁን በቅርቡ በቂ ዋስትና ሳይሰጣቸው ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ የተደረጉ ተፈናቃዮች በከፍተኛ ችግር ውስጥ ይገኛሉ” ሲሉ ሊቀመንበሩ ደብረጺዮን መግለጻቸውን የፓርቲያቸው ጽ/ቤት መረጃ አስታውቋል።
በአፍሪካ ህብረት የፕሪቶርያ ስምምነት የክትትል፣ ማረጋገጥ እና ማስከበር ተልዕኮ ኮሚቴ ሃላፊ ሁነው የተሾሙት ሜጀር ጀነራል ሳማድ አላዴ በበኩላቸው በተልዕኮው መሰረት መሬት ላይ ያሉ ሁኔታዎችን በመከታተል ሪፖርታቸውን እንደሚያቀርቡ በመግለጽ ከህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ጋር በጋራ እንደሚሰሩ መግለጻቸውመ መረጃው አመላክቷል።
ዶ/ር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል ለሜጀር ጄኔራል ሳማድ አላዴ መልካም የስራ ጊዜ በመመኘት ኮሚቴው ተልዕኮውን ለመወጣት በሚያደርገው ጥረት የህወሓት ትብብር እንደማይለየው መግለጻቸውን የጽ/ቤታቸው መረጃ ያሳያል።
የኢትዮጵያ መንግስት የፕሪቶሪያን ስምምነት “እየጣሰ ነው”፣ “የትግራይን ህዝብ እየገፋው ነው” ሲል ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ለአምስት ቀናት ሲያካሂደው የነበረውን የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ማጠናቀቁን ተከትሎ ሚያዚያ 4 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ማስታወቁን የተመለከተ ዘገባ ማቅረባችን የታወሳል።
ማዕከላዊ ኮሚቴው “ይህ አካሄድ መሻሻል አለበት ብሎ ያምናል” ያለው መግለጫው “የፕሪቶርያው ስምምነት ተከብሮ ሁለቱ ፈራሚዎች በፖለቲካዊ ውይይት እና መግባባት በጋራ መስራት አለባቸው የሚል እምነት እንዳለውም” ገልጿል፣ “እንደሁልጊዜው ዝግጁ መሆኔም ይታወቅልኝ” ማለቱም በዘገባው ተካቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ፤ አደረሰን

ሰማያት ተከፈቱ ፣ ምስጢርም ተገለጠ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዘመዷ ቅድስት...

አባቴ ለእኔ አባት ብቻ አልነበረም፤ ለእናቴ ታማኝ ባል፣ ለሁላችንም ደግሞ የደስታ ምንጭ ነበር

"አባዬ… ዛሬ ላለሁበት ማንነት መሰረት የሆንከኝ አንተ ነህ!" ​የአርቲስት...

የአንበሶቹ ትንሳኤ፦ የዳካር እንባ እና የቴራንጋ ድል

​በዳካር ሰማይ ስር ዛሬ ጨረቃ አልወጣችም፤ ይልቁንም በሚሊዮን የሚቆጠሩ...

የጥምቀት በዓል በመላ ሀገሪቱ በድምቀት እየተከበረ ነው

የጥምቀት በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እና በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት...