ህጋዊ መብትን መሰረት ያደረገው የትውልድ ጥያቄ

Date:

ኢትዮጵያ ለሺህ ዘመናት የባህር በር ባለቤት ሆና ኖራለች፡፡

በመሆኑም ባለፉት ዘመናት መርከቦቾ በየአቅጣጫው ሰፊ የንግድ እንቅስቃሴዎችን ያደርጉ አንደነበር የታሪክ ድርሳናት ያወሳሉ፡፡

ነገር ግን ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነቷን በውል ባልታወቀ ምክንያት እንድታጣ ተደርጓል።

ኢትዮጵያ በአንድ የታሪክ እጥፋት ያጣችውን የባህር በር ባለቤትነት አሁን ላይ ዋና አጀንዳዋ አድርጋ እየሰራችበት ትገኛለች፡፡

የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ የህልውና ጉዳይ መሆኑ የሀገሪቱ የምጣኔ ሃብት እድገትና የህዝብ ቁጥር መጨመር፣ የጂኦ ፖለቲካዊ ሁኔታ፣ የታሪክና የህግ ምክንያቶች ለአብነት ተጠቃሽ ናቸው።

የኢትዮጵያ ፍላጎት የባህር በርን በጋራ መጠቀምን ማዕከል ያደረገ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መግለፃቸው ይታወሳል፡፡

ሆኖም ግን የተሳሳተ ትርክትን በማራመድ ኢትዮጵያ የባህር በር እንዳታገኝ የሚታትሩ ባዳ እና ባንዳዎች አሉ፡፡

በአፍሪካ ቀንድ እና መካከለኛ ምስራቅ የሀይድሮ ፖለቲካል ተመራማሪ እና ተንታኝ ኢንጂነር ጥላሁን ኤርዲኖ (ዶ/ር) ከኢትዮጵያ ራዲዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ በባህር በር ጉዳይ ጠላቶች እያደረጉ ያሉት ድርጊት ስትራቴጂያዊ ጠላትነትን ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡

እነዚሁ አካላት ኢትዮጵያ ውስጥ የሀይማኖት እና የብሔር ግጭቶች በመፍጠር ሀገራችን እድትተራመስ ሲሰሩ መቆየታቸውንም ጠቅሰዋል፡፡

አካሄዷቸውም ኢትዮጵያ ተረጋግታ የኢኮኖሚ ልማቷን እንዳታፋጥን ማሰናከል መፍጠር መሆኑን ነው ያነሱት፡፡

በህዳሴ ግድብ ይነሱ የነበሩ ጥያቄዎች እና ወከባዎች ወደ ቀይ ባህር ዞሯል የሚሉት ተንታኙ፤ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ የምትጫወተው ታላቅ ሚና እና እየገነባች ያለው ኢኮኖሚ የታሪክ ጠላቶችን እረፍት የነሳ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በየአንዳንዱ የኢትዮጵያ ችግር ውስጥ እንደ ግብጽ ያሉ የታሪክ ጠላቶች እጃቸውን እደሚያስገቡም ነው የጠቀሱት፡፡

ከታሪክ በመማር እንደ ሀገር የተጠነሰሰብን ሴራ አንድነታችንን በማጠንከር ልናከሽፍ ይገባል ያሉት ተመራማሪው፤ የውስጥ ችግሮቻችን በመፍታት ብሄራዊ ጥቅማችንን ልናስጠብቅ ይገባል ብለዋል፡፡

Ebc

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ አዲስ አበባ ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ...

የቴሌኮም ኦፕሬተሮች የ5 በመቶ የአደጋ ሥጋት ምላሽ ፈንድ ክፍያን ተግባራዊ ማድረግ ጀመሩ

በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱት ሁለቱም የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ማለትም ኢትዮ ቴሌኮም እና...

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዚዳንት ለኢራን ህዝብ – “እኛ ከእናንተ ጋር ነን”

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዝዳንት ሮቤርታ ሜትሶላ፥ የኢራን መንግስት በተቃዋሚዎች ላይ...

አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና ሊኖራት ይገባል

በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አፍሪካ ቋሚ ውክልና...