የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ አዲስ የሥራ ሹመት የሰጡ ሲሆን፣ በዚህም መሠረት ሌተናል ጄነራል ጥጋቡ ይልማ የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሆነው ተሾመዋል።
በሌላ በኩል የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት ኮሚሽነር ጄነራል ዘላለም መንግሥቴ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ሆነው የተሾሙ ሲሆን፣ የክልሉ ፖሊስ መምሪያ ለሁለቱም ከፍተኛ አመራሮች መልካም የሥራ ዘመን ተመኝቷል።
