ለእናት ሀገር የገቡትን ቃል የጠበቁት የቤሉሉ መስዋዕት!

Date:

የመቶ አለቃ ተመስገን ረጋሳ

ከቀይ ባህር ጥግ አንስቶ ከቀኝ ወደግራ 3ቱ ብርጌዶች 48ኛ 49ኛና 50ኛ ብርጌዶች በስተመጨረሻ ግራ ጠርዝ መ/አ ተመስገን የሚመሩት የክ/ጦሩ ተወርዋሪ ሻለቃ መከላከል መስርተው ከያዙበት ሰፍራ አየተነሱ በተከታታይ ከፊት ለፊት ባለው ጠላት ላይ ከባድ ኪሳራን ያደረሱ ሲሆን በወቅቱ እዝያው በአሰብ ግንባር ተመድቦ የነበረው የአየር ሀይል አስኳድሮን ሚ24ና ሚ35 በተዋጊ ሄሊኮፕተሮች  ያደርጉ የነበረው ድጋፍ ከፍተኛ ነበር። በወርሃ ግንቦት17-1983 ዓ.ም የጀግናው ቃል ሊፈፀም ሰአታት ቀሩት።

ከጠላት መከላከያ ግንባር መስመር የቀላል መሳርያ ተኩስ አሩምታ ይሰማል እንጂ ምንም አይነት አንቅስቃሴ አይታይም ከወገንም የሚሰጥ ምላሽም አልነበረም። ተኩሱ የብስራት ይመስላል። አስመራ በሻዕብያ መያዙ የተሰማው አረፋፍዶ ነበር።ሁሉም በተጠንቀቅ ሆኖ የበላይ አካልን ተዕዛዝ ይጠባበቃል። ብርጌድ አዛዥ ፖለቲካና ደህንነት ሀላፊዎች ክ/ጦር መምርያ ለስብሰባ ተጠሩ ንጋት ላይ የጀመረው ተኩስ ጋብ ብሎ አልፎ አልፎ የታንክና መድፍ አረር ከጠላት ይወረወራል።

አመሻሽ ላይ ማጥቃት የሚመስል የተኩስ ልውውጥ ተጀመረ።ቀስ በቀስ የተኩስ ልውውጡ አየጋለ አየከረረ መጣ በተለይ መ/አ ተመስገን ይመሩት በነበረው ተወርዋሪ ሻለቃ ግንባር ውግያው ተጣጡፏል። ጀግናው መኮንን ተመስገን ረጋሳ ከግራ ወደ ቀኝ አየተሯሯጡ ጦሩን ያስተባብራሉ። በዚህ ሁኔታ ተውሎ ማውሻው ላይ ከበላይ አካል ጋር የነበረው የሬድዮ ግኑኝነት ከመቋረጡም ውጪ በሌሎች አጎራባች ክፍሎች ስለተፈጠሩ ሁኔታዎች ምንም መረጃ ማግኘት አልተቻለም።

መ/አ ተመስገን ቃል ለገቡላት እናት ሀገርም ሆነ ለጓዶቻቸው አበክረው ይናገሩ እንደነበረው ይመሩት የነበረውን ተወርዋሪ ሻለቃ በልበ ሙሉነት ሲያዋጉ በጠላት በተተኮሰ ጥይት ቆስለው ይወድቃሉ። መውደቃቸውን የተገነዘቡት የወገን ጦር አባላት በድጋፍ ወድኃላ ሊያወጧቸው ቢሞክሩም በሁሉም ግንባሮች ሁኔታዎች መበላሸታቸውን ለመረዳት በመቻላቸው መ/አ ተመስገን ጓዶቻቸውን እናንተ ውጡ እኔ አከተላችኋለው ይላሉ ጓዶቻቸውም እርስዎን ጥለን አንሄድም በማለት ያንገራግራሉ ጀግናው መኮንን ታጥቀውት የነበረውን ሽጉጥ ላጥ አድርገው በማውጣት ሄዱ ብያለሁ የኔ መጨረሻ እዚሁ ነው ብለው አፈጠጡ።

የመ/አ ተመስገን ሲስቁ ያስቃሉ ሲቆጡም ያስፈራሉ ትዕዛዛቸውን የተቀበሉት የወገን ጦር አባላት ጉዞዋቸውን ቀጠሉ። አፍታም ሳይቆይ ጀግናውን ትተው ጉዞ ከጀመሩበት አካባቢ የተኩስ ድምፅ ተሰማ በጉዞ ላይ የነበሩት አባላት በስተጀርባ ሲመለከቱ ጀግናው ቃላቸውን በመጠበቅ  እራሳቸውን መሰዋታቸውን ተገነዘቡ። በወጣትነት እድሜያቸው አሰብ ቤሉል በረሀ ላይ ለሚወዷት እናት ሀገር ፍቅር ተሰዉ!

ክብር ለዚች ታላቅ ሀገር መስዋዕት ለሆኑትም ሆነ ሀገራዊ ግዴታቸውን ለተወጡ ውድ የቀድሞው ሰራዊት አባላት በሙሉ ታሪክና ገድላችሁ በታሪክ ማህደር ውስጥ በደማቁ ተፅፎ ይኖራል። ፈለጋችሁን የተከተሉ ጀግኖች ዛሬም እናት ሀገር አፍርታለች!

ለሰራዊቱ ክብር በጠላት እጅ ላለመውደቅ ሰማዕት የኾኑት

ኮሎኔል አይተነው በላይ

በጎጃም ክፍለ ሀገር በሳር-ምድር ከተማ የተወለዱት ከፍተኛ መኮንን በ1946ዓ.ም የሆለታ ገነት ጦር ትምህርት ቤት ለ15ኛ ዙር ካስመረቃቸው እጩ መኮንኖች አንዱም ናቸው።

በቀድሞው ሰራዊት ውስጥ በተለያዩ ክፍሎች ያገለገሉ ሲሆን እንደ አርአያነት ከሚታዩባቸው ክፍሎች መካከል፦ በናዝሬት የታንከኛ ክፍል፣በመከላከያ ሚነስትትር የምድር ጦር በትምህርትና ማሰልጠኛ ሃላፊነት፣ በ3ኛ ክፍለ ጦር በጅጅጋ የታንከኛ አዛዥነት፣ በተጨማሪ ለመከላከያ ሚኒስቴር በዘመቻ መኮንንነት በሰሜን ዕዝ የ504ኛ ብርጌድ አዛዥነትና ለአብዮታዊው ዘመቻ መምሪያ በኢንስፔክተርነት አገልግለዋል። በተጨማሪ አሜሪካን ሀገር የታንክ አካዳሚ የአዛዥነትና አስተማሪነት ትምህርቶችን ተከታትለዋል። በተመድ የፀጥታ አስጠባቂነት ሀገራችንን ወክሎ ወደ ኮንጎ ከዘመተው ሰራዊት መካከል ይገኙበታል።

ኮ/ል ካሣ የ3 ንዑስ ግብረ ኃይሎች አዛዥ ሆነው ሳለ  የ503 “ለ” ንዑስ ግብረ ኃይል ብቻ ለሮራ-ፀሊሙ “ልዩ ግዳጅ”ሲመረጥ የተቀሩት ሁለቱ ግብረ ኃይሎች በዘመቻዉ ሳይሳተፉ የቀሩ ሲሆን በኮሎኔል ገበረክርስቶስ ቡሊ ክፋትና ተንኮል መሆኑ ይታወቃል።በወቅቱ ይህ ንዑስ ግ/ኃ ለግዳጅ የተነሳው ከምፅዋ በኢትዮጵያ ባህር ኃይል ምድረ ነክ (land craft) በመርሳ ጉልቡብ አርጎ ማዕሚዶ በመግባት ሮራ ፀሊም አጋት ተራራን ያለተሽከርካሪ ሁሉም በእግርና በሸክም በተደረገ ጉዞ ነዉ በጨበጣ ዉጊያ አጋት ከተያዘ በኋላ ይዞታዉን በማስፈትና የዉሃ ነጥብ በያዝ ለስንቅ፣ ጥቅና ቁስለኛ ማግለያ ሄሊኮፕተር ማሳረፍና መጠቃም የታቻለ ሲሆን የኦፕሬሽኑ ዋና ዓለማ የሆነዉን በአዶባህ ሸለቆ በኩል ሻዕቢያን ከናቅፋና አልጌና ጋር የሚያገናኘውን የግንኙነት መስመር በመቁረጥ አልጌናና ናቅፋ ለይ ኦፕሬሽን በመክፈት ጠላት አንዳይረዳዳ አድርጎ ነጥሎ ለመምታት ቢሆንም በአሻጥር ሁለቱ ግንባሮች ላይ የኦፕሬሽን ትዕዛዝ ሳይሰጥ እንዲቆይ በማድረግ ጠላት ያለ የሌለ ኃይሉን 503 “ለ” ግብረ ኃይል ላይ እንዲያጠናክር ዕድል የተሰጠዉ ሲሆን ግብረ ኃይሉ በተለይ የ20ኛ ብርጌድ በመከላከልና መልሶ ማጥቃት ለጠላት አልበገርም በማለቱ የተያዘውንውን ምሽግና የከፍታ ነጥብ በተጨማሪ የውሃ ነጥብ ቦታዉንም ጭምር አንድ ሻምበል ጦር ብቻ በመተዉ ወደ ሞተ መሬት (gorge) የወገን ጦር እንዲገባ በኮሎኔል ገ/ክርስቶስ ቡሊ ትዕዛዝ ተሰጠ።

የተሰጠውን ትዕዛዝ ጀግናው ኮ/ል ካሣ ገና ከጅምሩ ሁኔታዉን በማወቃቸው የአንገት ሀብልና ቀለበታቸውን ከአድራሻ ጋር ለሄሊኮፕር ፓይሌት በመስጠት የወገን ጦር በትዕዛዝ ወደ ሞት መሬት የገባ ሲሆን ጠላት ከፊትም ከኋላም ገዥ መሬት ይዞ ብዙ ፍልሚያ በጨበጣ ዉጊያ ጭምር ተደርጎ ብዙዎች ውድ ህይወታቸውን ከፍለዉ አልፈዉ ኦፕሬሽኑም ያለስኬት ሲጠናቀቅ ኮሎኔል አይተነው በላይም በዚሁ ግንባር እንደ ተቀሩት የአመራር አባላት ለአንዲት እናት ሀገር የገቡትን ቃል ለመጠበቅም ሆነ ለሰራዊቱ ክብር በጠላት እጅ ላለመውደቅ እራሳቸውን ሰዉተዋል!!!

ዘላለማዊ ክብር ስለ አንዲት እናት ሀገር በሰሜን ግንባር ደማቸውን ላፈሰሱ አጥንታቸውን ለከሰከሱ አብዮታውያን ጓዶች!!!

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫ በሚያካሂድባቸው ቦታዎች ሁሉ እሳተፋለሁ

በዘንድሮው ሀገራዊ ምርጫ እንደሚሳተፍ ያስታወቀው የኢትዮጵያ ዜጎች ለማሕበራዊ ፍትህ...

በሲዳማ ክልል ከ62% በመቶ በላይ የሚታረሰው መሬት በአሲዳማነት የተጎዳ ነዉ

በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ የሚታየው የምርታማነት ማነቆ በዋናነት የመሬት አሲዳማነት...

የኢትዮጵያ እዳ እና ሃብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን የሥራ ኃላፊዎች ስብሰባ ሳይገኙ ቀሩ

የመንግስት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ እዳ እና...

የኢትዮጵያ እና ሕንድ የቆየ ዲፕሎማሲዊ ግንኙነት

የኢትዮጵያ እና ሕንድ የቆየ ዲፕሎማሲዊ ግንኙነት የአፍሪካ-ሕንድ...