ሊባኖስ በእስራኤል ጦር ተመታች

Date:

እስራኤል በበርካታ የሊባኖስ አካባቢዎች ላይ ከባድ የአየር ጥቃት ሰነዘረች።

የእስራኤል አየር ሀይል  በመላ ሊባኖስ ጥቃት ማደረሱን ከቤይሩት የሚወጡ መረጃዎች ያሳያሉ።

ተዋጊ ጀቶቹ በቦዳኢ ከተማ በምስራቃዊ ሊባኖስ  ቢያንስ ሶስት ጥቃት ማድረሳቸው ተነግሯል።

ከባዓ’ልቤክ ባሻገር ተጨማሪ ሶስት ጥቃቶች በአርዚ እና ቡርጅ ራሃል ከተሞች በደቡባዊ ሊባኖስ ደርሰዋል፡፡

በሊታኒ ወንዝ እና በሌሎች በርካታ የደቡባዊ ሊባኖስ ክፍሎች ከባድ የአየር ጥቃት መፈጸሙን የቤይሩት ምንጮች አረጋግጠዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከጋዛ ወደ እስራኤል ሮኬት መወንጨፉ ተሰምቷል።

የእስራኤል ጦር ሮኬቱ በኪቡትዝ አቅራቢያ መውደቁን አረጋግጣል፡፡

የሃማስ ክንፍ  ቃሳም ብርጌድ በራጁም ሮኬቶች እስራኤል ላይ ጥቃት አድርሻለሁ ብሏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እስከ አምስት ዓመት እስራት የሚያስቀጡ የመረጃ ነጻነት አዋጅ ጸደቀ

ለ15 ዓመታት በስራ ላይ ከቆየው “የመገናኛ ብዙኃንና የመረጃ ነፃነት...

በደቡብ አፍሪካ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተላለፈ ማስጠንቀቂያ

በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኢምባሲ በሀገሪቱ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ እየተከታተለና...

በበጀት አመቱ 22.9 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ለማቅረብ እየተሠራ ነው

ከታቀደው 22 ነጥብ 9 ሚሊዮን ዶላር ኩንታል እስካሁን  20...

በቬንዝዌላ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ የ32 ሰዎች ህይወት አልፏል

በቬንዙዌላ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀ ሲሆን 7.2 እና 7.5...