ዘለንስኪ፤ በሩሲያ ላይ አዲስና ጠንካራ ማእቀብ ጥያለሁ አሉ

Date:

በማዕቀቡ 60 የሩሲያ ድርጅቶችና 73 ግለሰቦች ተካትተዋል

የዩክሬይኑ ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ፣ ዛሬ በቴሌግራም ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት መረጃ፣ በሩሲያ ላይ አዲስና ጠንካራ  ማእቀብ መጣላቸውን አስታውቀዋል፡፡

‹‹ማእቀቡ የሩሲያን የፋይናንስ ገቢ የሚያሽመደምድ ነው›› ያሉት ዘለንስኪ፤ ከእነዚህ ውስጥ በሩሲያ መንግስት የሚንቀሳቀስ የክሪፕቶ ከረንሲ እንደሚገኝበትም ገልፀዋል፡፡

በዛሬው ማእቀብ 60 የሩሲያ ድርጅቶችና 73 ግለሰቦች መካተታቸውንም አስረድተዋል፡፡

  ‹‹የሩሲያን ወታደራዊ ኢንዱስትሪ አቅም በዚህ መልኩ እንዲገደብ ካደረግነው ሩሲያ ይህንን ጦርነት እንድታቆም ማስገደድ እንችላለን›› ያሉት ዘለንስኪ፤ በሚቀጥለው ሳምንት በአውሮፓ ህብረት ሊወጣ የሚችለውን የሩሲያ ማእቀብንም በዩክሬይን ውስጥ ተግባራዊ እንደሚያደርጉት አስታውቀዋል፡፡

የአውሮፓ ህብረት እስካሁን 17 ጊዜ በሩሲያ ላይ ማእቀብ መጣሉ ይታወቃል፡፡ ለ18ኛ ጊዜ በሩሲያ ላይ የሚጥለውን ማእቀብ በተመለከተ በተደረገው ምክክር ስሎቫኪያ ተቃውሞ በማሰማቷ በድጋሚ ለመምከር ለሚቀጥለው ሳምንት ሌላ ቀጠሮ መያዙ ይታወቃል፡፡

የስሎቫኪያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ግን በሚቀጥለው ሳምንትም 18ኛው ማእቀብ ላይ እንደማይስማማ በመግለፅ ላይ ነው፡፡

(ዘ-ሐበሻ ዜና)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...

ከ 50 ሚሊዮን በላይ መራጮች በማንዋልና በዲጂታል ተመዝግበዋል

ከየካቲት 28_መጋቢት 28 የመራጮች ምዝገባ ሲካሄድ እንደነበር ይታወቃል። በተለያዩ ጉዳዮች...