ሐመረ ብርሃን የብራና መጻሕፍት ሥራ ድርጅት ላለፋት ዓመታት ለሀገራችን ኢትዮጰያ እና ለትውልዱ ላበረከተው ጉልህ አስተዋጽኦ እውቅና ተሰጠው ።
መቀመጫውን በሀገረ አሜሪካ በማድረግ ለዘመናት የሀገር ባለውለታዎችን እውቅና በመስጠት በሚታወቀው Society of Ethiopians Established in Diaspora (SEED)(ማኅበረ ዲያስፖራ በአሜሪካ) በMay 25, 2025 ሐመረ ብርሃን የ32ኛ ዓመት ልዩ ተሸላሚ የሆነ ሲሆን ሽልማቱን በሐመረ ብርሃን የአሜሪካ ማዕከል አስተባባሪ ወ/ሪት ገሊላ ዮሐንስ አማካኝነት ተቀብሏል።
ሐመረ ብርሃን ይኽ ክብር በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አምላክ ረድኤት፣ በሁሉም ቤተሰቦቻችን ተሳትፎ የመጣ በመሆኑ እንኳን ደስ አለን ለማለት ይወዳል።
