Home ዜና ሐማስ ለጋዛ ሰርጥ የቀረበውን አዲስ የተኩስ አቁም ሐሳብ ተቀብያለሁአለ

ሐማስ ለጋዛ ሰርጥ የቀረበውን አዲስ የተኩስ አቁም ሐሳብ ተቀብያለሁአለ

ሐማስ ለጋዛ ሰርጥ የቀረበውን አዲስ የተኩስ አቁም ሐሳብ ተቀብያለሁአለ

የንቅናቄው ኃላፊ ካሊል አል-ሐያ እስራኤል ስምምነቱን እንደማትጥስ ተስፋ እንዳላቸው ገልጸዋል።

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ቢሮ እስራኤል ከአሜሪካ ጋር በመስማማት በጋዛ የተኩስ አቁም ዙሪያ የራሷን የስምምነት ሐሳብ ለአሸማጋዮቹ ማቅረቧን ቅዳሜ ዕለት አስታውቋል።

እስራኤል ያቀረበችው ምትክ ምክረ ሃሳብ ከአሜሪካ ጋር ስምምነት እንደተደረሰበት ቢገለጽም፣ ምንም ምን ሃሳቦች እንደተካተቱበት የተባለ ነገር የለም።

አሜሪካ በጉዳዩ ላይ በይፋ አስተያየት አልሰጠችም።

እአአ ጥር 19 በሥራ ላይ የዋለው የተኩስ አቁም ስምምነት በዚህ ወር መጀመሪያ ካበቃ በኋላ የእስራኤል ኃይሎች በራፋ በእግረኛ ጦር ዘመቻ ሲጀምሩ፣ በጋዛ ሰርጥ ደግሞ የአየር ድብደባ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።

ሁለቱም ወገኖች የመጀመሪያው የተኩስ አቁም ስምምነት ካበቃ በኋላ ሁለተኛው ዙር ስምምነት ላይ መድረስ ሳይችሉ ቀርተዋል።

ሃማስ በመጀመሪያው የተኩስ አቁም ምዕራፍ 33 ታጋቾችን ለቅቋል።

በኢራን የሚደገፈው ቡድኑ አሁንም 59 እስራኤላውያን በቁጥጥሩ ስር ያሉ ሲሆን ከእነዚህ መካከል ሁሉም በሕይወት ይኖራሉ ተብሎ አይታመንም።