በትግራይ ክልል መቀለ አቅራቢያ የሚገኘው መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ከ75 ቀናት በኋላ ስሚንቶ ማምረት መጀመሩን አስታወቀ።
መስቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ በግብአት ማውጫ ሳይት (ኳሪ ሳይት) ላይ አጋጥሞት በነበረው ችግር ምክንያት ላለፉት 75 ቀናት ምንም አይነት ምርት እያመረተ እንዳልነበር ጠቆመ።
አሁን ላይ ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላትና የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ስምምነት ላይ በመደረሱ ወደ ምርት መመለሱን ከተቋሙ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
የመሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ሙሉ በሙሉ ለምርት ማቆሙ ዋነኛ ምክንያቴ ለስሚንቶ ምርት የምጠቀምባቸው የተለያዩ ጥሬ እቃዎች በተለያዩ ምክንያቶች በአግባቡ እና በወቅቱ ማግኘት ስላልቻልኩ ነው ሲል መግለጹን ሐምሌ 13 ቀን 2017 ዓ.ም ላይ ባቀረብነው ዘገባ መግለጻችን ይታወሳል።
ፋብሪካው የጥሬ እቃ በማወጣባቸው አከባቢዎች እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን በጊዜያዊነት እና በዘላቂነት ለመፍታት ከሚመለከታቸው መንግታዊ እና ማህበረሰባዊ አካላት ጋር በመመካከር ለመፍታት ጥረት ባደርግም እስካሁን መፍትሔ ማግኘት አልቻልኩም ማለቱም በዘገባው ተካቷል።
ነገር ግን ጥሬ እቃ በሚያወጣባቸው አከባቢዎች እያጋጠሙት ስላሉ ችግሮች በይፋ የገለጸው ነገር አልነበረም።
