መስማት ለተሳናቸው ዜጎች የመንጃ ፈቃድ ስልጠና መጀመሩ ተገለጸ

Date:

መስማት ለተሳናቸው ዜጎች የመንጃ ፈቃድ አገልግሎት እንዲያገኙ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን  የአዲስ አበባ ከተማ አሽከርካሪና ተሸከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን  አስታውቋል።

በባለስልጣኑ የተሸከርካሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ትዕግሥት አሰፋ መስማት የተሳናቸው ዜጎች የመንጃ  ፈቃድ ስልጠና እንዲያገኙ ጥያቄ ሲያቀርቡ እንደነበር አስታውሰዋል።  በመሆኑም መስማት የተሳናቸውን ዜጎች ጥያቄያቸው ምላሽ እንዲያገኝ  በባለስልጣን መሳሪያ ቤት የመንጃ ፈቃድ ስልጠና እንዲያገኙ ተፈቅዷ ሲሉ  ተናግረዋል።

በባለስጣኑ ውክልና በተሰጣቸው 1 መቶ 43 የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ስልጠና  ይሰጣል ሲሉ ገልፀዋል። 

የባለስልጣኑ የተሸከርካሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ትዕግሥት አሰፋ ስልጠናው ሲጠናቀቅ በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ፈተና እንደሚሰጥ ጠቁመዋል።

የሚሰጠው ፈተና የንድፈ ሃሳብ እናየተግብር ፈተና እንደሚያካትት የገለፁ ሲሆን፤ በአዲስ አበባ ከተማ አሽከርካሪና ተሸከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ቅርንጫፍየምዘና ማዕከል ይከናወናል ብለዋል።
(አሐዱ ራድዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ10 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ጥቅምት 12 ቀን 2019...

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ የፕላቲንየም ብራንድ የማስተር ካርድ ይፋ አደረጉ

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ደንበኞች የፕሪሚየም...

የአሜሪካ የደህንነት ኃላፊ ኢራንን አስጠነቀቁ

ቡሔራዊ ደህንነት ዳይሬክተር ጄይ ክላይተን አርብ ዕለት ኢራን በውጭ...

ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ  በአመት ከ1.1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ታጣለች

85 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ በግብርናው ዘርፍ የተሰማራ ሲሆን...