መንግስት ሰራተኞች ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የገንዘብ ብድር አወሳሰድ እና አመላለስ ሂደት

Date:

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለመንግስት ሰራተኞች  ያለ ምንም መነሻ ዋስትና በደመወዙ ልክ እስከ 150,000 ብር የዲጅታል ብድር አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ መመሪያ ማዘጋጀቱን ይታወሳል። 

ይህንን ገንዘብ ለመበደር የCEB Birr ተጠቃሚ መሆን የሚያስፈልግ ሲሆን፣ባንኩ ከደመወዝ ከፋይ ፋይናንስ ጋር በሚኖረውን ስምምነት መሠረት፣ ተበዳሪ አካል ባለበት ሆኖ፣በCEB Birr አማካይነት አገልግሎቱን የሚያገኝ ይሆናል።

ለዚህም የብድር አወሳሰድ እና አመላለስ ሂደት እንደሚከተለው ቀርቧል ።

👉 የግማሽ ወር ደመወዝ የሚበደር ሰው፣በአንድ ወር ውስጥ ተመላሽ የሚደረግ ሲሆን ፣ ወለድ 3% ይሰላል።

👉 የአንድ ወር ደመወዝ ሲበደሩ.. ወለድ 8% የመመለሻ ጊዜ 3 ወር፤

👉የሁለት ወር ደመወዝ ሲበደሩ..ወለድ 14% የመመለሻ ጊዜ 6 ወር፤

👉የሶስት ወር ደመወዝ ሲሆን፣ ወለድ 17% በዘጠኝ ወር፤

👉የአራት ወር ደመወዝ ለሚበደር ወለድ 20% በአንድ አመት።

ማነኛውም የመንግስት ሠራተኛ ያለምንም ማስያዣ፣በዲጂታል ሲስተም ብቻ ባለበት ሆኖ፣የብድር አገልግሎቱን ማግኘት የሚችል ሲሆን፣የደመወዝ መደበኛ ሂሳብ(account ) በስልክ ቁጥር (CEB Birr) የሚተካ ይሆናል።

ማነኛውም ተጨማሪ መረጃ የሚፈልግ ሰው  ይህንን አግልግሎት ወደ ጀመሩ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ በአካል በመገኘት በቂ መረጃ እና ማብራሪያ ማግኘት እንደሚቻል ይህንን የብድር አገልግሎት ከጀመሩ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...