MISS WORLD ETHIOPIA በመባል የሚዘጋጀውን አለም አቀፍ የቁንጅና ውድድር ላይ ለመሳተፍ ሞዴል ሀሴት ደረጀ የምትሄድ ሲሆን በቦሌ አለምዓቀፍ አየር ማረፊያ በቪአይፒ ሳሎን በክብር ተሸኝታለች።
ሞዴል ሀሴት ደረጀ በሜካኒካል ኢንጂነሪንግ ሁለተኛ አመት የአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጅ ተማሪ ናት።
ዘንድሮ በሕንድ ሃይድራባድ የሚዘጋጀውን ዓለምአቀፍ የቁንጅና ውድድር ከመቶ ሠላሳ ሃገሮች የሚሳተፉበት ትልቅ የቁንጅና ውድድር ሲሆን በዚህ ውድድር የኢትዮጵያን መልካም ገፅታ ለማስተዋወቅ መንግስት እየሰራ የሚገኘውን ስራ ከማስተዋወቅ አንፃር ለውጭ ዓለም ለማስተዋወቅ የሚረዳ ትልቅ ዓለም ዓቀፍ የቁንጅና ውድድር ነው፡፡
ይህ ዓለም ዐቀፍ የቁንጅና ውድድር ከ2014-2024 እ.ኤ.አ ድረስ ፕሮግራሙን ያዘጋጁት ተቋማት ኢትዮጲያ ቢዊቲ ኩንስ እና ፓሽን ፕሮሞሽን እና ኢቨንት ኃ/የተ/የግ/ማህበር በጋራ ያዘጋጁት አለም አቀፍ የቁንጅና ውድድር ነው፡፡
