የእስረኛ ልውውጡ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች አማካኝነት የተደረገ ነው ተብሏል፡፡
የሩሲያ ፌደራል ደህንነት አገልግሎት (FSB) የአሜሪካ ዜግነት ያላት ከሲና ካርሊናን በሩሲያው አርተር ፔተሮቭ መለዋወጣቸውን ገልጿል፡፡
ሩሲያ፤ ከአሜሪካ ጋር የተደረገውን የእስረኛ ልውውጥ እንዲሳካ አስተዋጽኦ ላባረከተችው አረብ ኤምሬትስ ምስጋና አቅርባለች፡፡
የሩሲያ ዜግነት ያለው ፔትሮቭ በፈረንጆቹ 2023 በግሪክ ሳይፐረስ በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ ነበር ወደ አሜሪካ በ2024 ተላልፎ የተሰጠው፡፡
ፔትሮቭ የተከሰሰው የተከለከሉ እቃዎችን በህገ ወጥ መንገድ (Export Control Act) በመጣስ ሲያዛዋውር በቁጥጥር ስር መዋሉን ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡
በሌላ በኩል ከሲና ካርሊና የአሜሪካና ሩሲያ ጥምር ዜግነት ያላት እንዲሁም የሎስ አንጀለስ ነዋሪ ስትሆን፤ በፈረንጆቹ 2024 በሩሲያ የካትሪንበርግ ከተማ ለዩክሬን ስትሰልል በቁጥጥር ስር መዋሏ ተመላክቷል፡፡
