Home ቢዝነስ ዜና ራይድ ትራንስፖርት ለደንበኞቹ ያቀረበው መኖሪያ ቤት

ራይድ ትራንስፖርት ለደንበኞቹ ያቀረበው መኖሪያ ቤት

ራይድ ትራንስፖርት ለደንበኞቹ ያቀረበው መኖሪያ ቤት

ኦቪድ ሪል እስቴት እና ራይድ ትራንስፖርት (Hybrid Designs PLC) በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የስራ ውል ስምምነት መፈራረማቸው በሳምንቱ ከተሰሙ ዜናዎች መካከል አንዱ ኾኗል፡፡ ኦቪድ ሪል እስቴት በኢትዮጵያ በተለይም በመዲናችን አዲስ አበባ የሚስተዋለውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ በሰፊው እየተንቀሳቀሰ ያለ ሪል እስቴት ሲሆን፤ ለአብዛኛው የማህበረሰብ ክፍል ጥራት ያላቸውን ቤቶች ገንብቶ ገቢን ባገናዘበ መልኩ በተመጣጣኝ ዋጋ በአጭር ጊዜ ውስጥ በማቅረብ አንቱታን አግኝቷል፡፡ አሁንም በርካታ ቤቶችን በመገንባት ላይ ትኩረቱን አድርጎ እየሰራ ይገኛል።

የኦቪድ ግሩፕ አካል የሆነው ኦቪድ ሪል እስቴት ለግንባታ የሚጠቀምባቸውን ግብአቶች ከእህት ኩባኒያዎቹ መረከቡ እና የአልሙኒየም ፎርም ወርክ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን መጠቀሙ የግንባታን ጊዜ እና ወጪ በእጅጉ በመቀነሱ ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸውን ቤቶች ለገበያ ማቅረብ አስችሎታል። ከዚህ ቀደም የገርጂ ዘመናዊ የመኖሪያ መንደርን ከፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ጋር በመተባበር በ18 ወራት ገንብቶ ያስረከበ ሲሆን፣ በተጨማሪም በልደታ፣ በሪቼ፣ በአዋሬ እንዲሁም በባህር ዳር ከተማ በርካታ ቤቶችን ገንብቶ በአጭር ጊዜ ውስጥ አስረክቧል።

ኦቪድ ሪል እስቴት ሁልጊዜም ለቃሉ ታማኝ በመሆን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለተጠቃሚዎች ቤቶችን ማስረከብ መርሁ አድርጎ የሚንቀሳቀስ ሲሆን፣ ይህንንም ለማስቻል ጠንካራ የሆነ አመራር በማዋቀር እና ጠንካራ የስራ ባህልን በሰራተኞቹ መካከል በመገንባት ቀን እና ሌሊት የሚተጋ ድርጅት ነው።

በአሁን ሰዓት የጫካ የቤቶች ፕሮጀክት፣ የኪንግስ ታወር ፕሮጀክትን እንዲሁም የኦቪድ ቦሌ ቡልቡላ ከተማ ፕሮጀክትን ይዞ እየሰራ የሚገኝ ሲሆን በኦቪድ ቦሌ ቡልቡላ ከተማ ፕሮጀክት ትምህርት ቤቶች፣ የጤና ተቋማት፣ የስፖርት ማዘውተሪያዎች እና የገቢያ ማዕከሎችን የያዘ ከ60,000 በላይ መኖሪያ ቤቶች ያሉት የማህበረሰቡን የመግዛት አቅም ያገናዘበ ዘመናዊ ከተማ በመገንባት ላይ ይገኛል። ይህንንም አላማውን ለማሳካት ኦቪድ ሪል እስቴት ከተለያዩ ጠንካራ ተቋማት ጋር በአጋርነት በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

በሌላ በኩል ለደንበኞቹ እና ለአሽከርካሪዎቹ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ የሚገኘው ራይድ ትራንስፖርት የአግልግሎት አድማሱን በየዘርፉ በማስፋት በHybrid Designs PLC ስር ከሚገኙ እህት ኩባንያዎቹ ጋር በጋራ በመሆን ደንበኞቹን፣ አሽከርካሪዎችን እንዲሁም በሰዋሰው መልቲሚዲያ ስር የሚገኙ የጥበብ ባለሙያዎችን የተሻለ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር ሲሰራ ቆይቷል።

የመኖሪያ ቤት እጦት የበርከታ ነዋሪዎች ችግር መሆኑን በመገንዘብም ለችግሩ የጋራ መፍትሄ ለመፈለግ የሚያስችሉጥናቶችን ከባለድርሻ አካላት ጋር ሲያከናውን ቆይቷል፡፡ በተለይም በከተማችን በአዲስ አበባ ችግሩ ጎለቶ የሚታይ ሲሆን ለዚህ መሰረታዊ እና አንገብጋቢ ጉዳይ በጋራ መፍትሄ ለማበጀት ተባብሮ መስራት ወሳኝ መሆኑን በማመን ከኦቪድ ሪል እስቴት ጋር በትብብር ለመስራት ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

የስምምነቱ አጠቃላይ ዓላማ ኦቪድ ሪል እስቴት በHybrid Designs PLC ስር ለሚገኙ ተቋማት የራይድ ቤተሰቦች የመኖሪያ ቤት ሽያጭ የዋጋ ቅናሽ አሰራርን አሰራርን በማመቻቸት የቤት ባለቤት ለመድረግና በአጠቃላይ የራይድ ቪሌጅ (የራይድመንደር) ለመገንባት ሲሆን ሀይብሪድ እና በስሩ ያሉ ተቋማትም ኦቪድ ሪል እስቴት ለሚያቀርባቸው የመኖሪያ ቤት ሽያጭ አገልግሎቶች የገበያ እንቅስቃሴዎችን በማከናወን የማስተዋወቅ ስራዎችን ከሌሎች እህት ተቋማቱ ጋር በጋራ በትስስር ለመስራት ተስማመተዋል፡፡ የስምምነቱን የተወሰኑ ነጥቦችን በዝርዝር ስንመለከት ፡-

• ኦቪድ ሪል እስቴት ለራይድ ትራንስፖርት፣ በስሩ ለሚገኙ እህትተቋማት እና ራይድ ቤተሰብ ዘመናዊ የመኖሪያ ቤቶችን በተመጣጣኝ የዋጋ ቅናሽ ለሽያጭ የሚያቀርብ ሲሆን በአጠቃላይ RIDE VILLAGE (የራይድ መንደር) ለመገንባት አስፈላጊውን እገዛ ያደርጋል፡፡

• ሀይብሪድ ዲዛይንስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር (ራይድ) ኦቪድ ሪልእስቴት ለአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር ለሚገኙ ደንበኞቹ ለሚያቀርበው የቤት ሽያጭ አገልግሎት የገበያ ንቅናቄውን በማስተዋወቅ ይስራል፣ ያሰተባብራል፡፡

• የራይድ ትራንስፖርት አሽከርከሪዎች ኦቪድ ሪል እስቴት ለሽያጭ ያዘጋጃቸውን ቤቶች በተሸከርካሪዎቻቸው እና በሌሎች የራሱ ፕላትፎርሞች የማስተዋወቅ ስራ ይሰራሉ፡፡

• በሰዋሰው መልቲ ሚዲያ በኩል የሚገኙ አንጋፋና ወጣት የጥበብ ባለሙያዎች፣ አርቲስቶች እና ከያኒያንን በማስተባበር ኦቪድ ሪል እስቴት የሚያቀርባቸውን አገልግሎቶችን እና የቤት ሽያጭ ንቅናቄዎችን ያከናውናል፡፡

• ሀይብሪድ ዲዛይንስ በቴክኖሎጂ የታገዙ የተለያዩ ፕላትፎርሞችን በመጠቀም የኦቪድን ምርትና አገልግሎት ማስተዋወቅ እና የኦቪድ ሪል እስቴትን የሚመለከቱ የምክክር ፎረሞችን በሚዲያ ያዘጋጃል፣

• በቀጣይም ሁለቱም ተቋማት ከላይ ለተጠቀሱት የራይድ ቤተሰቦች ምቹ እና ዘመናዊ መንደርን በመገንባትና በቴክኖሎጂ ትስስር የራይድ ቤተሰቦችን ህይወት ቀላል በማድርግ ረገድ የበኩላቸውን  አስተዋፅኦ ለማበርከት በትጋት የሚሰሩ ይሆናል፡፡

በአጠቃላይ ራይድ ትራንስፖርት ላለፉት ዓመታት ቁልፍ የሆኑ ስኬቶችን ማሳካት የቻለ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ፡-

• ዲጂታይዜሽን እቅዳችንን በተጠና መልኩ የተገበርንበት ፣

• የአሽከርካሪዎቻችንን እና የደንበኞቻችንን ደህንነት ከህግአስከባሪ አካላት ጋር በመተባበር በተሟላ መልኩ በስኬት ያስጠበቅንበት እንዲሁም አደጋን የተከላከልንበት፣

• የደንበኛን ምቾትና የአገልግሎታችንን ጥራት የሚያሳድጉ የተለያዩ ወሳኝ የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶችን እና አሰራሮችን በስኬት የከወንበት እና የGreen Initiative አካልየሆነውን Electric Vehicle አቅጣጫችንን ያሰመርንበት፣

• አጋር የRIDE አሽከርካሪዎች ጋር በስኬት ተናበን አለምአቀፋዊ ይዘቱን በጠበቀ መልኩ ፍፁም ቀናነት የተሞላበትCustomer Service የሰጠንበት ፣

• ትልቅ መሰረት የሚጥሉ ድርጅት ለድርጅት ግንኙነቶችንየመሰረትንበት እንዲሁም ፣

• ድርጅታችን በቀዳሚነት በሃገራችን ያስጀመረው የኤሌክትሮኒክ ትራንስፖርት አገልግሎት ደረጃውን በጠበቀ መልኩ በዲጂታል ስርአት ግብር እንዲከፍል ከባለድርሻ አካላት ጋር በጥምረት የሰራበት ውጤታማ ግዜ ነበር፡፡

———-

ቅጽ 6 ግዮን ቁጥር 216 ጥቅምት 2 ቀን 2017 ዓ.ም