
እንደ ይሁዳ ሁሉ ዛሬም የንፁሕ ደም የሚያፈስሱ፤ ንጹሕን አሳልፈው የሚሰጡ፤ እውነተኛውን ጻድቁን የሚያስገደሉትን ኢትዮጵያ መታቀፏን ብፁዕነታቸው ገልጸዋል፡፡
ንጹሕ ደም ማፍሰስ፤ ጻድቁን አሳልፎ መስጠት ምንም እንደማይጠቅም ከይሁዳ እንማር፤ በደላችንን አምነን አምለካችን ኾይ ማረን እንበለው ብለዋል፡፡
ይሁዳ ለራሱ ቢጎዳም ለእኛ ግን አስተምሮናል ነው ያሉት፡፡ እኛ ከይሁዳ መሻል አለብን፤ ዛሬ ላይ እንደ ይሁዳ ሰው የሚሸጥበት ዘመን ደርሰናል፤ “ሰውን በገንዘብ የሚሸጥ ትውልድ ይሁዳን ማማት አይችልም” ብለዋል። ከይሁዳ የተሻለ ትውልድ አልተገኘም፤ ከልብ ጸጸት የሌለበት፤ የከንፈር ብቻ ጽድቅ ያለበት ዘመን ነው ብለዋል፡፡
ሕሊናቸውን ለእግዚአብሔር የተሰጡ፤ ከዓለም የተገለሉ፣ ደጋግ ሰዎች ስላሉ በቸርነቱ እንኖራለን ነው ያሉት፡፡
በድያለሁ የሚለውን እንመን ያሉት ብጹዕነታቸው አምላክ በድለነው ሳለ ለእኛ መከራ ተቀብሏል፤ እኛ ግን በድለንም በድለናል አንልም ብለዋል፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀሉ ግርጌ እናት ሰጥቶናል፤ ያለ እናት አልተወንም ነው ያሉት፡፡ ስለ ሰላም እንጸልይ፤ ስለ ሀገራችን እንጸልይ፤ ክርስቲያን ስለ ዓለም ሁሉ ይጸልያልና ስለ ዓለም ሁሉ እንጸልይ፤ የተፈናቀሉትን እንዲመለሱ፤ ሰላም እንዲነግስ፤ ንጹሕ ደም መፍሰስ በቃ እንዲለን ተግተን እንጸልይ በማለትም ብፁዕነታቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡