ስለ ውንብድና ምን ያህል ያውቃሉ?
ውንብድና ማንም ሰው ተገቢ ያልሆነ ብልፅግና ለራሱ ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ የሌላው ሰው ንብረት የሆነውን ተንቀሳቃሽ እቃ ለመውሰድ እንዲያመቸው ወይም በሚወስድበት ጊዜም ሆነ ከወሰደ በኋላ የገጠመውን ተቃውሞ ለመቀልበስ በሌላ ሰው ላይ የሀይል ድርጊት መፈጸም ወይም ከባድ የሆነ የማንገላታት ተግባር ወይም ከባድ ዛቻ መፈፀም ወይም በማናቸውም ሌላ መንገድ ይህን ሰው ለመከላከል እንዳይችል ማድረግ የውንብድና ተግባር እንደሆነ በወንጀል ህጉ አንቀጽ 670 ላይ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ ይህን ወንጀል ፈፅሞ የተገኘ ሰው ከአስራ አምስት አመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት የሚቀጣ ይሆናል፡፡
ወንጀሉን የሚያከብዱ ሁኔታዎች (ከባድ ውንብድና)
በወንጀል ህጉ አንቀጽ 671 ላይ የውንብድና ወንጀልን ከባድ የሚያደርጉ ምክንያቶች የተዘረዘሩ ሲሆን ወንጀል ፈጻሚው ወንጀሉን የፈጸመው
• በሰዎች ላይ ወይም በንብረት ላይ የኃይል ተግባር ለመፈጸም በተቋቋመ የወንበዴ ቡድን አባል በመሆን ሲሆን
• ተበዳዩን እገልሀለሁ ብሎ እርግጠኛ የሞት አደጋ እንደሚደርስበት በመዛት፣ በጦር መሳሪያ ወይም በተለይ አደገኛ በሆነ ሌላ አይነት መሳሪያ በማስፈራራት ወይም ስቃይ በሚያደርስ ሁኔታ በማንገላታት ወይም ከባድ የአካል ጉዳት በማድረስ ሲሆን
• አደገኝነቱን በሚያሳይ በማናቸውም ሌላ ሁኔታ ሲኾን ወንጀል ፈጻሚው ከአምሰት ዓመት እስከ ሃያ አምስት አመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ሊቀጣ ይችላል፡፡ በሌላ በኩል ወንጀል ፈጻሚው ወንጀሉን የፈጸመው ወንጀል ለመፈጸም ከተደራጀ ቡድን ጋር በመሆን ወይም የጦር መሳሪያ ወይም ሌላ አደገኛ መሳሪያ በመያዝ የህዝብ ጸጥታን አደጋ ላይ የሚጥል ወይም የተለየ ጨካኝነት የሚያሣይ ዘዴን በመጠቀም፣ ወይም የተፈጸመው የሀይል ተግባር ዘላቂ የአካል ጉዳትን ወይም ሞትን ያስከተለ ሲሆን ቅጣቱ እድሜ ልክ እስራት ሲሆን የውንብድና ወንጀል አፈጻጸሙ እጅግ ከባደ በሆነ ጊዜ የሞት ቅጣት ሊሆን እንደሚችል የወንጀል ህጉ ደንጎት ይገኛል፡፡ የጦር መሳሪያን በመጠቀም በቡድን በመሆን በልማደኝነት የውንብድና ወንጀልን መፈጸም በሞት እንደሚያስቀጣ የወንጀል ህጉ አንቀጽ 671 በግልጽ ደንግጎት ይገኛል፡፡
ጠቅላላ ዕውቀት
ከ12 ሚስቶች 102 ልጆች እና 568 የልጅ ልጆች ያዩት የ67 አመት አርሶ አደር በጤና እጦት እና በገቢ ማነስ ምክንያት መውለድ አቁሚያለው አሉ፡፡ ሙሳ ሃሳህያ በኡጋንዳ ዋና ከተማ ካምፓላ ውስጥ ሉሳካ የሚባል ቦታ ነዋሪ ናቸዉ። ከ12 ሚስቶች 102 ልጆች እና 568 የልጅ ልጆች ያዩት የ67 አመት አርሶ አደር በጤና እጦት እና ገቢዬ ከኑሮ ውድነቱ አንጻር በመዳከሙ ሰፊውን ቤተሰብ የሚቀላቀሉ ተጨማሪ ልጆች እንዳይኖሩ አድርጓል” ብለዋል። ሚስቶቻቸውም እንዳይፀነሱ የወሊድ መቆጣጠሪያ እንዲጠቀሙም አዘዋል። በኑሮ ውድነቱ ሳቢያ ገቢዬ እየቀነሰ መጥቷል በዚህም ሰፊውን ቤተሰቤን ማኖር አልቻልኩም ሲሉ ከዘ ሰን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ምሬታቸውን ገልጸዋል። ዕድሜያቸው ከስድስት እስከ 51 ዓመት የሆናቸው አብዛኞቹ የሃሳህያ ልጆች እንደ መኖሪያ ቦታቸው በሚያገለግለው እርሻው ውስጥ አብረው እንደሚኖሩ ተዘግቧል። ሚስቶቹ ጥቂቶቹ ወጣት ሴቶች ሲሆኑ ትልቁ ልጃቸው ከወጣቷ ሚስታቸው በ21 አመት እንደሚበልጥ ተነግሯል።
ድንቃይ
በህንድ የምትኖር የ80 አመት አዛውንት ላለፉት 68 አመታት አሸዋ እና ጠጠር ተመግባለች፡፡ ኩሽማ ቫቲ ከቫራናሲ የተባለች በህንድ የምትኖር የ80 አመት አዛውንት ላለፉት 68 አመታት አሸዋ እና ጠጠር ምግቧ እንደሆነ ተናገረች። የ15 ዓመት ልጁ እያለሁ ነበር የሆድ ድርቀት በሽታ ያጋጠመኝ ይህንኑ ለማስታገስ በመጀመሪያ አሸዋ እና ጠጠር በላሁኝ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ አሸዋ እና ጠጠር ምግቤ ሆነዋል ስትል ትናገራለች፡፡ ብዙ ሰዎች ይህ እንግዳ የሆነ አመጋገብ በጤና ላይ ሊያመጣ የሚችለውን የጎንዮሽ ጉዳት ይጨነቃሉ እሷ ግን “አሸዋ እና ጠጠር ማኘክ ጥርሶቼን በጣም ጠንካራ አድርጓቸዋል” ትላለች፡፡ “ለ 68 ዓመታት አሸዋ እና ጠጠር እየበላሁ ነው፣ እነሱን መብላት እወዳለሁ እና ምንም አይነት ጉዳይ አላስከተሉብኝም “ ብላለች፡፡ ቫቲ ልጆቼ እና የልጅ ልጆቿ እንዳቆም ቢሞክሩም በአሸዋ ውስጥ ያሉት ማዕድናት ጤንነቴን ጠብቀውታል በማለት አሻፈረኝ ብላለች፡፡ “የልጅ ልጆቼ ከዚህ ሱስ ለመገላገል የህክምና እርዳታ እንዳገኝ አጥብቀው ነግረውኛል ነገር ግን ምንም የሚያስፈልገኝ አይመስለኝም፣ ጤናማ ነኝ እናም ለደህንነቴ ጠባቂ ለሆነው ለአሸዋ ምስጋና ይግባው ትላለች፡፡ ቫቲ “ከ 15 ዓመቴ ጀምሮ ሀኪም አላየሁም፣ ፍጹም ጤነኛ ነኝ በአሸዋ ውስጥ ያሉት ማዕድናት ጉልበት እንደሚሰጡኝ ይሰማኛል ማለቷን የዘገበው ላይፍ ነው።
ከእንስሣት ዓለም
ፍሎሲ ኬንት የተባለች ድመት በአለማችን ረጅም ዓመት በመኖር ጊነስ ወርልድ ሪከርድስ ላይ ሰፍራለች፡፡ ድመቷ በፍሎሪዳ የምትኖር ሲሆን ወደ 27 ዓመት የሚጠጋ ዕድሜ እንዳላት ተረጋጋጧል፡፡ በዚህም በዕድሜ አንጋፋና ረጅም ድመት የኖረች ‘ልዩ ድመት’ አድርጓታል፡፡ ፍሌሲ በፊት 22 ዓመት ዕድሜ ከነበረው ጂኖዎልፍ ከተባለ በአሜሪካ ነዋሪ ውሻ በ4 ዓመት በመብለጥ ነው የጊነስ ወርልድ ሪከርድን የሰበረችው፡፡ በጊነስ ወርልድ ሪከርድስ የ27 አመት እድሜ የሚጠጋ ድመት ከእንግሊዝ የዓለማችን አንጋፋ ድመት ተብላ ተመርጣለች። ጊነስ ወርልድ ሪከርድስ እንዳረጋገጠው ፍሎሲ በታህሳስ 29 ቀን 1995 እ.ኤ.አ እንደተወለደች የተረጋገጠ ሲሆን አሁን 26 አመት ከ316 ቀናት በላይ መኖሯን አረጋግጫለሁ ብሏል። ፍሎሲ “የማየት እና መስማት ችግር ያለባት ቢሆንም በጥሩ ጤንነት እንደምትገኝ ተገልጿል፡፡ ፍሎሲ በዚህ ወር የአለም ክብረወሰን ያስመዘገበ ብቸኛ የቤት እንስሳ አለመሆኗን ፎክስ ኒውስ ዘግቧል።
