በእነ አቶ ጌታቸው ረዳ የተቋቋመው ዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ (ስምረት) የፓለቲካ ፓርቲ ዋና ፅህፈት ቤቱ በመቐለ ከፈተ።
በተጨማሪም ፓርቲድ የመቐለ እና ደቡባዊ ምስራቕ ዞን ቅርንጫፍ ቢሮዎች ከፍቷል።
ፓርቲው እንዳስታወቀው ዋና ፅህፈት ቤቱ በመቐለ በመክፈት የፓለቲካ ስራውን በግልፅ ጀምሯራ።
ፓርቲው በሁሉም የትግራይ የዞን ፣ የወረዳና ከተሞች ፓለቲካዊ ፅህፈት ቤቶች መክፈት እንደሚቀጥል አስታውቋል።
ከአንድ ወር በፊት ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ቅድመ እውቅና ያገኘው ስምረት ፓርቲ ለምስረታ ብቁ የሚያደርጉት አባላት መልምሎ ጨርሷል።
የክልል ፓርቲ ለመመስረት የሚስፈልገው 4 ሺህ በላይ መስራች አባላት መልምሎ ለይፋዊ ምስረታ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ተነግሯል ።
ስምረት ፓርቲ በቀጣዩ የነሀሴ ወር 2017 ዓ.ም በትግራይ ይፋዊ ምስረታ በማከናወን ከቅድመ እውቅና ወደ ሙሉ እውቅና እንደሚሸጋገር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
