አለልኝ አዘነ በሰዉ እጅ ስለመገደሉ ፍርድ ቤቱ አረጋገጠ

Date:

በእግር ኳስ ተጫዋቹ አለልኝ አዘነ ግድያ ላይ በሁለት ፈረቃዎች የፍርድ ውሳኔ ለመስጠት የተሰየመው የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ።

1ኛ ተከሳሽ የአለልኝ ባለቤት እና 2ኛ ተከሳሽ የባለቤቱ እህት ባል መጋቢት 17 ቀን 2016 ዓ/ም ከሌሊቱ 5፡30 እስከ 8 ሰዓት ገደማ ባለዉ ጊዜ በአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር ነጭ ሳር ቀበሌ ልማት ሰፈር ‘ ሃይላንድ ‘ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በተቀነባበረ ሁኔታ የ26 አመቱን ወጣት በመግደል ።

እራሱን ያጠፋ እንዲመስል በማድረግ የግዲያ ወንጀል መፈፀማቸው በሰውና በሰነድ ማስረጃዎች በመረጋገጡ ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛ ብሏቸዋል ።

ከሰዓት በኃላ የፍርድ ውሳኔ ለመስጠት ቀጠሮ ይዞ የነበረዉ የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት መደበኛ ችሎት የዐቃቤ ሕግና የተከሳሾችን ጠበቃ የቅጣት አስተያየት ካደመጠ በኋላ ዉሳኔዉን ወደ ሀምሌ 15/2017 ዓ/ም አሸጋግሯል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...