በሀዋሳ የቅዱስ ገብርኤል ንግስ በተቋቋመ ጊዜያዊ ችሎት አንድ ግለሰብ በ3 ዓመት እስራት ተቀጣ

Date:

በሀዋሳ ከተማ አየተከበረ ባለው ዓመታዊ የቅዱስ ገብርኤል ንግስ በዓል በተቋቋመ ጊዜያዊ ችሎት አንድ ግለሰብ በሦስት ዓመት እስራት ተቀጣ።

ግለሰቡ ዛሬ ማለዳ ስልክ ነጥቆ ሊያመልጥ ሲል በቁጥጥር ስር መዋሉን የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀልና ትራፊክ አደጋ ኃላፊ ኢንስፔክተር ሽመልስ ብሩ ተናግረዋል።

ከንግስ በዓል ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ የጸጥታና ህገ ወጥ ድርጊቶችን ለመከላከልና ህግን ለማስከበር ከትላንት ከሰዓት ጀምሮ ጊዜያዊ የምድብ ችሎት ተቋቁሞ እየሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል።

በዚህም የተቋቋመው ጊዜያዊ ችሎት ግለሰቡ የፈጸመውን ወንጀል አጣርቶ የሦስት ዓመት እስራት እንደተፈረደበት ማወቅ ተችሏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...