በማንችስተር ደርቢ የኳታር የጸጥታ ሀይሎች ይሳተፋሉ

Date:

ዛሬ ምሽት 12:30 ላይ በታላቁ ኦልድ ትራፎርድ ስታዲየም በሚደረገው የማንቹሪያን ደርቢ ላይ የኳታር የጸጥታ ሀይሎች በደህንነት ስራ ላይ እንደሚሳተፉ ተነገሯል።

የማንቹሪያን ደርቢ ጨዋታ ተጠባቂ ሲሆን ባለሜዳዉ ማንችስተር ዩናይትድ ወደ ወራጅ ቀጠናዉ ዝቅ ላለማለት ለሲቲዝኖቹ ደግሞ የሻምፒዮንስ ሊግ መግቢያ ቦታ ለማግኘት የሚያደርጉት ጨዋታ ይሆናል።

ምንም እንኳ ማንችስተር ዩናይትድ ከታላላቅ ቡድኖች ጋር በሚያደርገዉ ጨዋታ ጠንካ መሆኑን ደጋግሞ ቢያሳይም ከነበረበት የከፍታ ደረጃ ከወረደ ግን አመታት ተቆጥረዋል። ዩናይትድ በማንቹሪያን ደርቢ የበላይነት የያዘዉ ቡድንም ነዉ።

በደርቢዉ ጨዋታ ላይ በማንችስተር ሲቲ በኩል ኤርሊንግ ሃላንድ በጉዳት የማይገኝ ሲሆን ዩናይትድ ማቲያስ ዲሊግትን እንደሚያጣዉ ተዘግቧል።

በጽጥታ ስራዉ ላይ ይሳተፋሉ ለተባሉት የኳታር የጸጥታ ሀይሎችም የማንችስተር ከተማ ፖሊስ ገለጻና መመሪያ ሰጥቷቸዋል።

 

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...