የጉራጌ ዞን ስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት መምሪያ ባዘጋጀዉ ባዛርና ኤግዚቢሽን ላይ የኢንተርፕራይዞችና የግል አንቀሳቃሾች ስራዎቻቸዉ ይዘዉ ቀርበዋል።
በዚህ ባዛር ላይ ይህ ወደ ቤት መኪና የተቀየረቸችዉ ባጃጅ አንዱ የኤግዚቢሽኑ ድምቀት ነበረች።
የባጃጁን የሞተሩን ክፍል ተጠቅሞ የቤት መኪና የሰራዉ ወጣት ተመስጌን ሀብታሙ እንደሚለዉ የቤት መኪናዉ ወጪ ቆጣቢና ከጸሀይና ዝናብ መከላከል የሚያስችል እንደሆነም ተናግሯል።
የቤት መኪናዉ በአንድ ሊትር ቤንዝል 15 ኪሎ ሜትር የሚጓዝም እንደሆነ አመላክቷል።
የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን
