በሴቶች 3 ሺህ ሜትር የተወዳደሩት ዮርዳኖስ ጽጋብ እና ሽቶ ጉሚ 1ኛ እና 2ኛ በመሆን ውድድራቸውን አጠናቀዋል።
ዮርደዳኖስ ጽጋብ የውድድሩ አሸናፊ ስትሆን ርቀቱን ለማጠናቀቅ 8:43.65 ወስዶባታል።
ሽቶ ጉሚ 8:45.06 በሆነ ጊዜ 2ኛ በመሆን የብር ሜዳሊያ ስታገኝ፣ ዩጋንዳዊቷ ቻሪቲ ቼሮፕ 3ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሯን አጠናቃላች።
ይህ ውድድር ትናንት በሴቶች 3000 ሜትር መሰናክል ከተመዘገበው የወርቅ ሜዳሊያ በኋላ በዓለም ከ20 ዓመት በታች ሻምፒዮናው የተገኘ 2ኛው ወርቅ ሆኗል ።
