በዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና የተሳተፈው ኢትዮጵያ ልዑክ አቀባበል ተደረገለት

Date:

በቻይና ናንጂንግ በተካሄደው 20ኛው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ ገብቷል።

የልዑካን ቡድኑ አባላት ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የጀግና አቀባበል የተደረገላቸው መሆኑን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ መረጃ አመላክቷል።

ለልዑካኑ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴዔታ መኪዩ መሃመድ፣ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች አቀባበል አድርጎላቸዋል።

ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው 2 የወርቅ እና 3 የብር ሜዳሊያዎችን በማግኘት ከዓለም 3ኛ እንዲሁም ከአፍሪካ 1ኛ በመሆን ማጠናቀቋ ይታወቃል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...