በዲጂታል ምህዳሩ የሚፈጸሙ ማጭበርበሮች 180 በመቶ ጨምረዋል

Date:

የማንነት ማረጋገጫና የኮምፒሊያንስ አገልግሎቶችን የሚሰጠው Sumsub የተባለዉ  ዓለማቀፍ ኩባንያ  አዲስ ባወጣው የማንነት ማጭበርበር ሪፖርቱ መሰረት፣ ምንም እንኳን ዓለም አቀፍ የማጭበርበር ሙከራዎች አጠቃላይ መቀዛቀዝ ቢያሳዩም፣ የሳይበር ወንጀለኞች ሰዉ ሰራሸ አስተዉሎትን (AI) በመጠቀም የሚሰነዘሩት የማጭበርበር ጥቃቶች በከፍተኛ ደረጃ እያደጉ መጥተዋል፡፡

እ.ኤ.አ በ2025 አጠቃላይ የማንነት ማጭበርበር ሙከራዎች መጠነኛ ቅናሽ (ከ2.6% ወደ 2.2%) ቢያሳዩም፣ በሰዉ ሰራሽ አስተዉሎትና በጥልቅ ማታለል (deepfake) የሚሰሩ እጅግ የተራቀቁ የማጭበርበር ሙከራዎች 180 በመቶ መጨመራቸዉን ሪፖርቱ አመልክቷል።

ሪፖርቱ፤ የተረጋጉ የሚመስሉ አጠቃላይ የጥቃት መጠኖች አደጋውን የሚደብቁ መሆኑንና እያንዳንዱ ስኬታማ የማጭበርበር ሙከራ አሁን ላይ ከፍተኛ ጉዳትና ረጅም ጊዜ የሚቆይ ተጽዕኖ እንደሚያስከትል ማስጠንቀቁን የINSA ዲጂታል መረጃ ጠቁሟል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...