በዶ/ር ይሹሩን አለማየሁ አዴ የተዘጋጁት ሁለት አዳዲስ መጽሐፎች ለንባብ በቁ

Date:

የቀድሞው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ዴኤታ እና አሁን ላይ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ተመራማሪና ምሁር ዶ/ር ይሹሩን አለማየሁ አዴ (PhD) ያዘጋጇቸው ሁለት አዳዲስ መጽሐፎች በዛሬው እለት በቤስት ዌስተርን ፕላስ ሆቴል በይፋ ተመርቀዋል።

በዛሬው እለት ለዕይታና ለንባብ የበቁት ሁለቱ መጽሐፎች Architecting the Future: A Blueprint for the Next Human Civilization እና Introduction to Astronautics: A Beginner’s Guide የተሰኙ ናቸው::

የመጀመሪያው Architecting the Future: A Blueprint for the Next Human Civilization የተሰኘው መጽሐፍ የሰውን ልጅ ማዕከል ያደረገ፣ በቴክኖሎጂ የተደገፈና በዕሴቶች ላይ የተመሠረተ ሥልጣኔን ለመገንባት የሚያስችል አርቆ አሳቢ ዕቅድ (Blueprint) እንደሚያቀርብ የተገለፀ ሲሆን መጽሐፉ የፈጠራ ሥራዎች፣ ሥነ-ምግባር፣ አመራርና ሥርዓታዊ አስተሳሰቦች ለዛሬው ዓለም አቀፋዊ ፈተናዎች እንዴት መፍትሔ ሊሆኑ እንደሚችሉ የሚተነትን ነው።

ሁለተኛው Introduction to Astronautics: A Beginner’s Guide መጽሐፍ ደግሞ ስለ ስፔስ (ህዋ) እና አስትሮኖቲክስ አስደናቂ ዓለም ቀላልና ማራኪ ማብራሪያ የሚሰጥ ሲሆን፤ ውስብስብ የሆኑ የህዋ ሳይንስ ጽንሰ-ሀሳቦችን፣ የስፔስ ተልዕኮዎችን፣ የሮኬቶችንና የህዋ ምርምር መርሆችን ለጀማሪዎች፣ ለተማሪዎችና ለዘርፉ ሰዎች በሚመጥን መልኩ የሚያብራራ እንደሆነ ተነግሯል።

የመጽሐፉ ደራሲ ዶ/ር ይሹሩን አለማየሁ አዴ እንደገለጹት የመጀመሪያው Architecting the Future መጽሐፍ የዛሬው ዓለም ከፍተኛ ለውጥ እያጋጠመው መሆኑንና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፣ ሮቦቲክስ፣ ኳንተም ኮምፒውቲንግ፣ ባዮቴክኖሎጂ፣ የጠፈር ቴከኖሎጂ፣ ዲጂታል ኢኮኖሚ እና ዘላቂ የልማት ስርዓቶች የሰው ልጅን የኑሮ ዘይቤ በፍጥነት እየቀየሩት ነው።እነዚህ ቴከኖሎጂዎች እድልም ናቸው፤ ፈተናም ናቸው፡፡

ስለዚህ የወደፊቱን ዓለም በቴክኖሎጂ ብቻ ሳይሆን በሥነ-ምግባር፣ በሰብዓዊ እሴቶች፣ በፍትሕ፣ በአካታችነት እና በዘላቂነት መመራት እንዳለበት ያብራራል ብለዋል።

ይህም መጽሐፍ ለመንግሥታት የፖሊሲ አቅጣጫ፣ ለዩኒቨርሲቲዎች የምርምር ራዕይ፣ ለኢንዱስትሪ የፈጠራ አቅጣጫ፣ ለወጣቶች ደግሞ የህይወት መነሳሳት እንዲሆን ታስቦ ተዘጋጅቷል ተብሏል።

ዶ/ር ይሹሩን አክለውም ሁለተኛው Introduction to Astronautics መጽሐፍ የተፃፈው የጠፈር ሳይንስን ለማስተማር ብቻ አይደለም፤ ወጣቶች “እኔም በዚህ ዘርፍ መሳተፍ እችላለሁ” የሚል እምነት እንዲኖራቸው ለማድረግ ነው ብለዋል፡፡

በተጨማሪም በመጽሐፉ ውስጥ የሮኬት ሳይንስ፣ የምህዋር ሜካኒክስ፣ ሳተላይቶች፣ የጠፈር ተልዕኮዎች፣ የጠፈር ሮቦቲከስ፣ የጠፈር ህግ፣ የጠፈር ኢኮኖሚ እና የጠፈር ዲፕሎማሲ በተግባራዊ መልኩ መቅረባቸውን ገልጸዋል።

በተለይም ኢትዮጵያና አፍሪካ በአዲሱ የጠፈር ኢኮኖሚ ውስጥ ተመልካች ሳይሆኑ ንቁ ተሳታፊ መሆን እንዳለባቸው መጽሐፉ በግልጽ ያብራራል።

የመጽሐፍቱ አላማ ወጣቶችን ወደ STEM እንዲገቡ ለማነሳሳት፣ በኢትዮጵያ የምርምርና የፈጠራ ባህል እንዲጠናከር፣ በዩኒቨርሲቲዎች ውይይት እንዲፈጥሩ፣ ፖሊሲ አውጪዎች የረጅም ጊዜ ስትራቴጂከ አስተሳሰብ እንዲያዳብሩ፣እንዲሁም ኢትዮጵያ በሳይንስና በቴከኖሎጂ የሚመራ አገር እንድትሆን የእውቀት አስተዋፅኦ ለማድረግ እንደሆነ በመርሀግብሩ ተጠቁሟል።

በዚህ ታላቅ የመጽሐፍት የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ ምሁራን፣ የልማት አጋሮች፣ ተማሪዎችና የፈጠራ ባለቤቶች ታድመዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢራን ጠቅላይ መሪ ለአባታቸው ግድያ “የበቀል እርምጃ” እንደሚወሰድ ተናገሩ

የኢራን ጠቅላይ መሪ ሞጅታባ ኻሜኒ በጽሑፍ ባስተላለፉት መልዕክት አባታቸው...

የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የመጨረሻ ልምምዱን ሰርቷል

ቡድኑ ነገ የአለም ዋንጫ ማጣሪያ የመጨረሻ ዙር የመልስ ጨዋታውን...

ኢራን ከአሜሪካ ጋር ለመደራደር አለመጠየቋን አስታወቀች

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኢስማኤል ባጋይ፤ አገራቸው...

ሱዳን ዉስጥ ለሦስት ዓመታት የተካሄደው ጦርነትን ሰለ ማቆም

የሱዳን ብሔራዊ ጦር ለሦስት ዓመታት የተካሔደውን ጦርነት ለማቆም አሜሪካ...