በጋምቤላ ክልል ወርቅ አዉጪ ድርጅቶች የነዳጅ እጥረት እንዲፈጠር ምክንያት ሆነዋል ተባለ

Date:

በክልሉ ያለዉ የነዳጅ ግብይት ህግ እና ስርአትን ተከትሎ እየተከወነ አይደለም ተብሏል።

በዚህም በክልሉ ሰዉ ሰራሽ የነዳጅ እጥረት በመከሰቱ በማህበረሰቡ እንቅስቃሴ ላይ እክል መፍጠሩን ከክልሉ ንግድ ቢሮ ሰምተናል።

የጋምቤላ ክልል ንግድ ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ኛሞች ጊል በክልሉ ያሉ የነዳጅ ማደያዎች ከተለያዩ የወርቅ አዉጪ ድርጅቶች ጋር እየፈፀሙት ያለዉ ህገ ወጥ ግብይት ዋነኛ ችግር ሆኗል ብለዋል።

ማደያዎች ያመጡትን ናፍጣ እና ቤንዚል ከታሪፍ በላይ ከመሸጣቸዉ በተጨማሪ ነዳጅ በድብቅ በጥቁር ገበያዉ እየወጣ መሆኑ ተገልጿል።

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በክልሉ የማደያ ግንባታዎች መበራከት ተስተዉሏል።

በዚህም ፍቃድ ሰጪ ተቋማት የአስፈላጊነት ግምገማዎችን በማድረግ በህጋዊ ስርአት ብቻ ፍቃድ ሊሰጡ እንደሚገባቸዉ ተጠይቋል።

የክልሉ ንግድ ቢሮ በህገ ወጥ የነዳጅ ችርቻሮ ላይ የተሰማሩ ማደያዎች እና ግለሰቦች ለመቆጣጠር እርምጃዎች እየተወሰዱ መሆኑን ገልጿል።

የነዳጅ እጥረት እንዲፈጠር እያደረጉ ነዉ በተባሉ ማደያዎች በመቆጣጠር የነዳጅ ስርጭቱን  ማስተካከል እንዲቻል እየተሰራ መሆኑም ተገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግብጻዊቷ የቴሌቪዥን አዘጋጅ በዕፅ ዝውውር ወንጀል የሞት ፍርድ ተወሰነባት

የካይሮ የወንጀል ችሎት፤ ዕውቋን የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ ሳራ ካሊፋን...

ከአሜሪካ ጋር የሚኖረው “የጨዋታው ሕግ ተቀይሯል፤ የተመጣጠነ ምላሽ ዘመን አብቅቷል

ኢራን ከአሜሪካ በኩል ለሚሰነዘርባት ጥቃት የምትሰጠው ተመጣጣኝ የአጸፋ ምላሽ...

የ2.5 ቢሊየን ብር ግዙፍ ፕሮጀክት በአታ ለማርያም ገዳም በመስከረም ወር የመሠረት ድንጋይ ሊያኖር ነዉ

​በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ የታዕካ ነገሥት...

የዲቪ ዕድለኞች የማመልከቻ ሂደታቸውን እንዲቀጥሉ ተወሰነ!

የአሜሪካ የፌዴራል ፍርድ ቤት በዲቪ ሎተሪ አመልካቾች የማመልከቻ ሂደት...