
በዛሬው ዕለት ሊካሄዱ የነበሩ የጣልያን ፕሮፌሽናል እግርኳስ ጨዋታዎች በሙሉ መሰረዛቸው በይፋ ተገልጿል።
ጨዋታዎቹ የተሰረዙት የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስን ህልፈተ ህይወት ተከትሎ መሆኑ ይፋ ተደርጓል።
የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ በ88 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን ቫቲካን አሳውቋል።
ይህንንም ተከትሎ አራት የጣሊያን ሴርያ እና አስር የሴሪ ቢ ጨዋታዎች ለሌላ ጊዜ መተላለፋቸው ተገልጿል።