📌 አሜሪካ፡ ትራምፕ በጥቃቱ ሙከራ መደናገጣቸውንና መቆጣታቸውን የገለጹ ሲሆን፣ ይህም አሜሪካ ከዘለንስኪ ጋር በምትሠራው ሥራ ላይ ተጽዕኖ እንደሚኖረው ተናግረዋል።
📌 ቻይና፡ ቤጂንግ በፑቲን መኖሪያ ላይ የተሰነዘረውን ጥቃት ተከትሎ ግጭትን ከሚያባብሱ ድርጊቶችና ትንኮሳዎች መቆጠብ እንደሚያስፈልግ አሳስባለች።
📌 ፓኪስታን፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ሸህባዝ ሻሪፍ በኤክስ ገጻቸው ላይ “እንዲህ ዓይነቱ ጥቃት ለሰላም፣ ለደህንነት እና ለመረጋጋት ‘ከባድ ስጋት’ ነው” ብለዋል።
📌 ሕንድ፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ሀገራቸው “በሩሲያ ፕሬዝዳንት መኖሪያ ላይ የተሰነዘረው ጥቃት በጣም እንዳሳሰባት ” ተናግረዋል።
📌 ካዛክስታን፡ የካዛክስታን ባለስልጣናት የዩክሬንን ጥቃት አውግዘዋል፤ ፑቲን እና ቶካዬቭ በስልክ መነጋገራቸውን ክሬምሊን አስታውቋል።
📌 ባህሬን፡ የዩክሬን ጦር ኃይሎች በፑቲን መንግስታዊ መኖሪያ ላይ ለማጥቃት ያደረጉትን ሙከራ ባህሬን ያወገዘች ሲሆን፣ ለሩሲያ ፕሬዝዳንት ያላትን ድጋፍ ገልጻለች።
📌 ኡዝቤኪስታን፡ ፕሬዝዳንት ሚርዚዮዬቭ ከፍተኛ ቁጣቸውን የገለጹ ሲሆን፣ “የኪዬቭ አገዛዝ የሚፈጽመውን ግድ የለሽ ድርጊት” ማውገዛቸውን ክሬምሊን አስታውቋል።
📌 ቱርክሜኒስታን፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ጥቃቱ በተለይም ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች በሚደረጉበት ወቅት ዓለም አቀፍ ደህንነትን አደጋ ላይ የሚጥል ነው ብሏል።
📌 አብካዚያ፡ ፕሬዝዳንት ጉንባ “እንዲህ ዓይነቱ የኪየቭ አገዛዝ እብደት የመጨረሻ የሞት ጣር እንጂ ሌላ ሊባል አይችልም” ብለዋል።
📌 የተባበሩት የአረብ ኤምሬቶች፡ “ኤምሬትስ በክቡር ቭላድሚር ፑቲን መኖሪያ ላይ የተቃጣውን የጥቃት ሙከራ አጥብቃ ታወግዛለች” ያለች ሲሆን፣ “ደህንነትን እና መረጋጋትን ለማናጋት የታለሙ ማናቸውንም የጥቃት ዓይነቶች” ውድቅ አድርጋለች።
📌 ኢራን፡ ፕሬዝዳንት መስዑድ ፔዜሽኪያን በኪዬቭ አገዛዝ የተደራጀውን መጠነ-ሰፊ የድሮን ጥቃት አውግዘዋል።
📌 ሞስኮ በፑቲን መኖሪያ ላይ በኪዬቭ የተፈጸመውን ጥቃት ላወገዙ የውጭ ሀገር ወዳጆቿ እና አጋሮቿ ምስጋናዋን ታቀርባለች ሲሉ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ላቭሮቭ ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
