ባለሀብቶች በመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚገኙ ማሽኖቻቸውን ከሀገር ለማስወጣት ጥያቄ አቀረቡ

Date:

#በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ በሚገኘው ኢንዱስትሪ ፓርክ የተሰማሩና ጦርነትን ሸሽተው ከሀገር የወጡ ባለሀብቶች ማሽኖቻቸውን ከሀገር ለማስወጣት ጥያቄ ማቅረባቸውን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ።

የኮርፖሬሽኑ የኦፕሬሽንና ማኔጅመንት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ካሚል ኢብራሂም እንደተናገሩት በጦርነት ወቅት ከአገር ሸሽተው የሄዱ ባለሀብቶችን ለረዥም ጊዜያት በኢንተርኔትና በአካል በመገናኘት ኩባንያዎቻቸው ተመልሰው ወደ ልማት እንዲገቡ ጥረቶች ቢደረጉም ፍላጎት አለማሳየታቸውን ገልጸዋል፡፡

“በአጠቃላይ አገራዊ ምርት የተመዘገቡ ማሽኖችን ወደ ሌላ አገር ከሚወስዱ፣ በአገር ውስጥ ወደ ሌላ አካባቢ  በማዘዋወር ለማሠራት ጥያቄ አቅርበን እየጠበቅን ነው” ሲሉ የኮርፖሬሽኑ የኦፕሬሽንና ማኔጅመንት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ካሚል ኢብራሂም ተናግረዋል።

ወ/ሮ ሶስና ጌታሁን የተባሉ የቋሚ ኮሚቴው አባል በበኩላቸው፣ መቀሌ የነበሩ ኢንቨስተሮች እዚያው መቆየት ካልፈለጉ ወደ ሌሎች አከባቢዎች ለማዘዋወር የቀረበውን ጥያቄ ተችተዋል፤ “ኢንቨስተሮቹ ቦሌ ለሚ ወይም አዳማ እንዲያለሙ ለማድረግ እየተሠራ ነው የሚለው ምላሽ ተገቢ አይደለም” ማለታቸው ተጠቁሟል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...