ባለሃብቱ በላይነህ ክንዴ ለበዓል መዋያ የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ

Date:

በላይነህ ክንዴ ግሩፕ ዛሬ ባሰራጨው መረጃ መሠረት፣ “በቡሬ ከተማ የሚገኘው ፊቤላ ኢንዱስትሪያል ስራ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ለአካባቢው ማህበረሰብ የሚበጁ ማህበራዊ ሀላፊነቶችን በመወጣት ላይ ይገኛል።”

“ፊቤላ ባለፉት 4 ዓመታት ከ200 በላይ የሚሆኑና በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩ ወገኖችን በቋሚነት በየወሩ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ” የገለጸው ቢኬጂ ግሩፕ፣ “ፊቤላ በቋሚነት ከሚያደርገው ድጋፍ በተጨማሪ በዓላትን መነሻ በማድረግ በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ወገኖችም ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል። የፊታችን እሁድ የሚከበረውን የፋሲካ በዓል ምክንያት በማድረግ ከ1300 በላይ ለሚሆኑና በቡሬ ከተማ ለሚገኙ ወገኖች ድጋፍ አድርጓል።” ሲል ገልጿል።

በተያያዘ ዜና በላይነህ ክንዴ ፋውንዴሽን በአዲስ አበባ ከተማ በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ወገኖችም ድጋፍ ማድረጉን ገልጿል።

ፊቤላ ኢንዱስትሪያል፣ ባለፉት አራትላአመታት በቡሬ ከተማና አካባቢው ከገንዘብ ድጋፍ በተጨማሪ የትምህርት ተቋማትና የውሃ መሠረተ ልማት በመገንባት፣ የጤና መድህን በመክፈል፣ በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ወገኖችን ቤት ገንብቶ በማስረከብ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ላይ እንደሚገኝ ካሰራጨው መረጃ ላይ ተመልክተናል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አቶ ይህንዓለም አቅናው የአማራ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆኑ

በኢትዮጵያ በፍጥነት እያደጉ ከሚገኙ እና ከፍተኛ የባለአክስዮኖች ቁጥር ካላቸው...

ማዕቀቦች የኢራንን የኒውክሌር መርሃ-ግብር ቢያደናቅፉም መንግስቱን ሊጥሉ እንደማይችሉ ተገለጸ

ማዕቀቦች የኢራንን ወታደራዊ እና የኒውክሌር እንቅስቃሴዎች አስቸጋሪና ውድ እንዲሆኑ...

የአፍሪካ ሀገራት አዲስ የኢንቨስትመንት ፈንድ ይፋ አደረጉ

በአፍሪካ ሀገራት ላይ የተደቀነውን ከፍተኛ የብድር ጫና ለማቃለል እና...

ዶናልድ ትራምፕ “በቅርቡ” ሆርሙዝ የአሜሪካ ግዛት አካል እንደሚሆን ተናገሩ

ከኢራን ጋር ያለው ግጭት እየተባባሰ ባለበት በአሁኑ ሰዓት የአሜሪካው...