ባለፉት ሶስት ወራት ከ3ሺ በላይ የፍቺ ምዝገባ ተከናውኗል

Date:

የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የ1ኛ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት እንደሚያመላክተው በሩብ ዓመቱ 3ሺ32 የፍቺ ምዝገባ መከናወኑን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ንጉሴ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

በሩብ ዓመቱ በወሳኝ ኩነት ምዝገባ 153ሺ787 ልደት ምዝገባ ተከናውኗል። 25ሺ876 ህፃናት በተወለዱ በዘጠና ቀናት ውስጥ  የተመዘገቡ ሲሆን 4ሺ194 ደግሞ በአንድ ዓመት ውስጥ የተመዘገቡ  መሆናቸውን  ተናግረዋል።

በተጨማሪም 10ሺ696 ጋብቻ በሩብ ዓመቱ ተመዝግቧል።እንዲሁም 100 የጉዲፈቻ ምዝገባ መከናወኑን ገልፀዋል።

4ሺ396 የሞት ምዝገባ በወቅታዊ፣በዘገየ እና የጊዜ ገደቡ ባለፈ ተመዝግቧል ።እንደ አጠቃላይ በበጀት ዓመቱ የ1ኛ ሩብ ዓመት ውስጥ 172ሺ011 ምዝገባ በማድረግ ከእቅድ በላይ ማከናወን መቻሉን አቶ ዮሴፍ ንጉሴ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...

በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መፈጸም አይጠበቅባቸውም

አሜሪካ እና ኢራን በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ...

እስራኤል ጦሯ በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እንደተናገሩት፤ በአሜሪካ እና በኢራን...