ቤንጃሚን ኔታንያሁ ለቀረበባቸው የሙስና ክስ የይቅርታ ጥያቄያቸውን

Date:

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ለቀረበባቸው የሙስና ክስ የይቅርታ ጥያቄያቸውን ለሐገሪቱ ፕረዚደንት አቀረቡ። ኔታንያሁ  ለፕሬዚደንቱ ያቀረቡት የይቅርታ ጥያቄ በእሳቸው ላይ የተመሰረተውን የሙስና ወንጀል ክስ እንዲሰረዝላቸው ነው።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅሕፈት ቤት  እንዳስታወቀው  በቤንጃሚን ኔታንያሁ የተመሰረተው የሙስና ክስ ሐገሪቱን ክፉኛ መከፋፈሉንና ረዥም ጊዜ የወሰደው የክስ ሂደት ዶሴ መዘጋቱ ለሐገሪቱ ብሔራዊ አንድነት እንደሚጠቅም ገልጿል።

የአሜሪካው ፕረዚደንት ዶናልድ ትራምፕ እስራኤልን በጎበኙበት ወቅት የእስራኤል ፕረዚደንት አይዛቅ ሔርዞግ ለኔታንያሁ ምህረት እንዲያደርጉ ጠይቀው ነበረ። ከሳምንታት በፊትም ትራምፕ ለእስራኤል ፕረዚደንት በላኩት ደብዳቤ ይህን ጥያቄያቸውን በድጋሚ አቅርበዋል።

የኔታንያሁ የይቅርታ ጥያቄ ግን ከሐገሪቱ ተቃዋሚዎች ብርቱ ነቀፌታን አስከትሏል። ጥያቄው የሐገሪቱን የዴሞክራሲ ተቋማትን የሚያዳክምና እሳቸው ከሐግ በላይ መሆናቸውን የሚያሳይ አደገኛ መልእክት የሚያስተላልፍ ነው የሚል ትችት ተቃዋሚዎች ሰንዝረዋል።

DW Amharic

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ደቡብ ሱዳን የነዳጅ ቅድመ-ክፍያ ውሎችን እንዳትፈጽም አገደ

የለንደን ፍርድ ቤት ደቡብ ሱዳን ከአሁን በኋላ አዳዲስ የነዳጅ...

” ከ140 በላይ ጠጠር አምራች ድርጅቶች ሙሉ በሙሉ ቆመዋል ” – ማህበሩ

" ካላቸው ቅሬታ ማቅረብ ይችላሉ። ግን መሬቱ መቼ እንደተወሰደባቸው...

ትራምፕ “በኢራን ላይ ሊፈጸም ታቅዶ የነበረውን ጥቃት አንፈጽምም” አሉ

ትራምፕ በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ ቁልፍ የአሜሪካ አጋር ሀገራት መሪዎች...

በነዳጅ ጭማሪ በኬንያ በተቀሰቀሰ ተቃውሞ የአራት ሰዎች ሕይወት አለፈ

በኬንያ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪን ተከትሎ በዋና ከተማዋ ናይሮቢ በጸጥታ...