ቬንዙዌላ እና ኢራን አሁንም በርካሽ ዋጋ ቀዳሚ ናቸው

Date:

እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር የ2026 መጀመሪያ ላይ በወጡ መረጃዎች መሠረት፣ በዓለማችን እጅግ ርካሽ የነዳጅ ዋጋ የሚገኝባቸው ሀገራት ዝርዝር ውስጥ ኢራን እና ቬንዙዌላ አሁንም የመሪነቱን ቦታ ይዘዋል።

በኢራን አንድ ሊትር ቤንዚን በ0.02 ዶላር (ሁለት ሳንቲም) ገደማ እየተሸጠ ሲሆን፣ በቬንዙዌላ ደግሞ ዋጋው በ0.03 ዶላር (ሦስት ሳንቲም) አካባቢ ይገኛል።

ቬንዙዌላ በዓለም ትልቁ የነዳጅ ክምችት ያላት ሀገር ብትሆንም፣ በሀገሪቱ ባለው የፖለቲካ አለመረጋጋት እና በቅርቡ ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ በአሜሪካ ልዩ ኃይሎች በቁጥጥር ስር መዋልን ተከትሎ፣ ይህ እጅግ ዝቅተኛ የሆነ የነዳጅ ድጎማ ይቀጥላል ወይስ ይቆማል የሚለው ጉዳይ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ እጅግ ርካሽ ነዳጅ የሚሸጥባቸው አምስት ሀገራት፦

1) ኢራን ($0.02/ሊትር)
2) ሊቢያ ($0.03/ሊትር)
3) ቬንዙዌላ ($0.035/ሊትር)
4) ኩዌት ($0.28/ሊትር)
5) አልጄሪያ ($0.31/ሊትር)

በአንጻሩ በሆንግ ኮንግ እና በአንዳንድ የአውሮፓ ሀገራት የአንድ ሊትር ነዳጅ ዋጋ እስከ 3.70 ዶላር ድረስ እንደሚሸጥ መረጃዎች ያመለክታሉ።

የቬንዙዌላ የነዳጅ ዘርፍ በአሜሪካ ኩባንያዎች ድጋፍ ዳግም እንዲያንሰራራ የሚደረገው ጥረት፣ በቀጣይ ወራት በዓለም አቀፍ የነዳጅ ገበያ ላይ የዋጋ ቅናሽ ሊያስከትል እንደሚችል የኤኮኖሚ ባለሙያዎች ይገምታሉ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ10 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ጥቅምት 12 ቀን 2019...

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ የፕላቲንየም ብራንድ የማስተር ካርድ ይፋ አደረጉ

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ደንበኞች የፕሪሚየም...

የአሜሪካ የደህንነት ኃላፊ ኢራንን አስጠነቀቁ

ቡሔራዊ ደህንነት ዳይሬክተር ጄይ ክላይተን አርብ ዕለት ኢራን በውጭ...

ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ  በአመት ከ1.1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ታጣለች

85 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ በግብርናው ዘርፍ የተሰማራ ሲሆን...