ትራምፕ ከኢራን ጋር ስምምነት ባይደረስም ጦርነቱ በሁለት ወይም በሦስት ሳምንት ውስጥ እንደሚያበቃ ተናገሩ

Date:

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ በኢራን ላይ የከፈተችው ጦርነት ከሁለት እስከ ሦስት ሳምንት በሚሆን ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል አሉ። ኢራን ስምምነት ላይ መድረሷ ጦርነቱን ለማቆም ቅድመ ሁኔታ አለመሆኑንም ገልጸዋል።

ትናንት በዋይት ሃውስ ከጋዜጠኞች ጋር ቆይታ ያደረጉት ትራምፕ፤ አሜሪካ “እጅግ በቅርቡ” ከኢራን ጋር የገባችበትን ጦርነት እንደምታቆም ጠቁመዋል። አሜሪካ የምትወስደው ወታደራዊ እርምጃ “በሁለት ወይም ሦስት ሳምንት” ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ሲናገሩ ተደምጠዋል።

እንደ ፕሬዝዳንቱ ገለጻ፤ አሜሪካ ከአንድ ወር በፊት ከእስራኤል ጋር በመሆን ጥቃት ከመክፈቷ በፊት ያስቀመጠቻቸውን ግቦች አሳክታለች። ዋነኛው ግብ የኢራንን የኒውክሌር መሣሪያ የመታጠቅ አቅም መገደብ እንደነበር የተናገሩት ትራምፕ፤ አሜሪካ አሁን “ስራውን እያጠናቀቀች” መሆኑን አንስተዋል።

አሜሪካ የአራንን ሰማይ እንደተቆጣጠረችው እንዲሁም በበርካታ ከፍተኛ ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ አመራሮች ግድያ ምክንያት የአገዛዝ ለውጥ መሳካቱንም ተናግረዋል። አዲሶቹን የኢራን አመራሮች ከቀድሞዎቹ አንጻር “አክራሪነታቸው እጅጉን የቀነሰ” እንዲሁም “ይበልጥ ምክንያታዊ” ሲሉ ገልጸዋል።

የኢራን መሪዎች አሜሪካ ጦርነቱን እንድታበቃ የሚያደርጋት “ስምምነት ላይ ለመድረስ እየለመኑ” ነው ሲሉም ከዚህ ቀደም ኢራን ያስተባበለችውን ንግግራቸውን ደግመዋል።

እንደ ትራምፕ ገለጻ ከኢራን ጋር ስምምነት ባይደረስም ጦርነቱ ሊቋጭ ይችላል። “ኢራን ስምምነት ላይ መድረስ አይጠበቅባትም። ከእኔ ጋር ስምምነት መፈጸም አይጠበቅባቸውም” ሲሉ ተናግረዋል።

በፓኪስታን በኩል ባለ 15 ነጥብ የስምምነት እቅድ ወደ ኢራን የላኩት ፕሬዝዳንት ትራምፕ፤ ቴህራን እነዚህ ነጥቦች የማትቀበል ከሆነ ወታደራዊ እርምጃቸውን እንደሚጨምሩ ሲዝቱ ቆይተዋል።

በስምምነት እቅዱ ላይ ከተቀመጡ ዋነኛ ነጥቦች መካከል፤ ኢራን የኒውክሌር መሣሪያ እንደማይኖራት ቃል እንድትገባ ማድርግ እና ሁሉንም የዩራኒየም ማበልጸግ ተግባሯን እንድታቋርጥ ማድረግ የሚሉት ይገኙበታል።

የሆርሙዝ ወሽመጥ ሙሉ በሙሉ መከፈቱም ከስምምነት እቅድ ነጥቦች መካከል ነው። ከዓለም የነዳጅ ምርት 20 በመቶ ያህሉ የሚተላለፍበት ይህ ወሳን የባሕር ጉዞ መስመር በመዘጋቱ እና በጦርነቱ ምክንያት በኢነርጂ መሠረተ ልማቶች ላይ በደረሰው ጉዳት የተነሳ በዓለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል።

ትራምፕ በትናንቱ ንግግራቸው አሜሪካ ወታደራዊ እርምጃ መውሰድ እንዳቆመች ጦርነቱ በነዳጅ ዋጋ ላያ የፈጠረው ተጽዕኖ እንደሚረግብ ገልጸዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...