ናኒ ጤናው ዘውዴ

Date:

የታይኳንዶ የጥቁር ቀበቶ ባለቤትና የግል አሰልጣኝ

“መንፈሳዊ ስሜትና አካላዊ እንቅስቃሴ በጤና ለመቆየት በጣም ውጤታማ መንገዶች ናቸው፡፡ የነገ ሴቶች በመጪው ብሩህ ዘመናቸው ማሳካት የሚፈልጉት ጉዳይ በተመለከተ በፍጹም ቸል ማለት የለባቸውም” ስትል ናኒ “Coffee Memories Magazine” ከሚባል መጽሔት ጋር ቃለ መጠይቅ አድርጋለች።

የማርሻል አርትስ ጥናት በተመለከተ ምን ያህል እናውቃለን? ሰዎችስ ወደዚህ ጥበብ እንዴት ይገባሉ? ብዙዎቻችን ማርሻል አርትስ ሲባል ስለትግል የሚያጠና ጥበብ ነው ብለን እናምናለን፡፡ በአሁኑ ግዜ ከእነዚህ ሁለት ተፎካካሪ ተቃርኖዎች አንጻር ቅይጥ ማርሻል አርትስ ተደርጎ ይታያል፡፡ አንዳንዴ የዋሻ ትግል /cage fighting/ በመባል ይጠራል፡፡ ይህ ጥበብ እንደ ካራቴ፣ ዩ-ጂትሱና ቦክስ በመሳሰሉት የትግል ስፖርት ዓይነቶች የሚተገበሩ ቴክኒኮችን ያካትታል፡፡

ዘመናዊና መንፈሳዊ የማርሻል አርትስ ጥበብ “ዘ ብሎም” (Z.Bloom) በተባለ ጸሐፊ የተጻፈ አንድ ጽሑፍ ማንበቤን አስታውሳለሁ፡፡ ማርሻል አርትስ በሁለት ይከፈላል ይላል ጸሐፊው፡፡

አንደኛው አንድ ግለሰብ ወይም ስፖርተኛ  በተቃራኒ ካለው ግለሰብ ወይም ስፖርተኛ ጋር የስልጠናው አካል በሆነው እንቅስቃሴ የሚተገበር  ሲሆን ጨካኝ የግጭት ማስወገጃ ዘዴ ተብሎ ይጠራል፡፡

“ዘመናዊ አሰለጣጠን ወይም የጥናት ዓይነት” በመባል የሚጠራው ይህ ዓይነቱ የማርሻል አርትስ ጥበብ ከግዜ ወደግዜ ዘመናዊ ለውጥ በማሳየት ላይ ይገኛል፡፡ ለተለማማጆች ደግሞ እራሳቸው ብቁ መሆናቸውን የሚያረጋግጡበት ዕድል ይሰጣቸዋል፤ ለአካላቸውና ፍላጎታቸው የሚሆኑ የውስጥ ክህሎትና ልዩ ዘይቤ እንዲያዳብሩ ይረዳቸዋል፡፡

ከዚህ የመጀመሪያ ጥናት በተጨማሪ ሁለተኛው ጥናት ከማርሻል አርትስ ምንጭና ጥንታዊ ታሪክ የሚነሳ ነው፡፡ ይህም “መንፈሳዊ የጥናት ዓይነት” በመባል የሚጠራ ሲሆን በተለይ መንፈሳዊ እድገት ለጤና እና ለአካል ብቃት አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝና መታገያ መንገድ ሳይኖር ሲቀር ለሰልጣኞች እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡ ይህ ደግሞ እኔን እውቅና ያላት፣ በታይኳንዶ የጥቁር ቀበቶ ባለቤትና የግል አሰልጣኝ ወደ ሆነችው ናኒ ዘንድ ይወስደኛል፡፡

እዚህ ጋር ግንኙነት እንዳለ ማየት እችላለሁ፡፡ በማርሻል አርትስ ያላት ተሳትፎ ሌሎች ሴቶችን መንፈሳዊ ክፍሎች ለማዳበር ፣ ከቤተሰቧ አስተዳደግና የግል ፍላጎቶች አንጻር ከ“መንፈሳዊ የጥናት ዓይነት” ጋር ተዛምዶ እንዳለው ይሰማኛል፡፡

እኔ ለሰልጣኞች በተለይ ሴቶች አእምሯቸውንና አካላቸውን ለማዳበር፤ እራስን መቆጣጠር የሚስችላቸውን /women’s self-control/ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አስተምራለሁ፡፡

“እንደ መሪ ማንንም ከማሰልጠን በፊት ይህንን መተግበር የእኛ ኃላፊነትና ግዴታ መሆኑ ይሰማኛል፡፡” ትላለች የ 28 ዓመት ዕድሜ ያላት ናኒ ጤናው ዘውዴ፡፡ ናኒ በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ሳይንስ ዲግሪ ያላት ሲሆን በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂም ሌላ ዲግሪ ይዛለች፡፡ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ትምህርትን ከቴክኖሎጂ ጋር በማቀናጀት የተደራሽ መጠን ከፍ ለማድረግና ለማስፋት በማሰብ ነው ሁለቱን ትምህርቶች ያጠናችው፡፡ ከኢንተርኔት መፈጠር በፊት ትንሿ ናኒ እንደ ጃኪ ቻን እና ጀት ሊ የመሳሰሉት አለማቀፍ ፊልም ኮከቦች ተጽእኖ እንዳሳረፉባት ታስታውሳለች፡፡

ናኒ ያላትን ችሎታ እና እውቀት ለሕጻናት በማካፈል መስራት ጀመረች፡፡ ሰባት ዓመት በአካል ብቃት እንቅስቃሴ አሰልጣኝነት የሰራችው ናኒ በሙያዋ የዕድገት መገለጫ ላይ አንድ ነገር ጨመረችበት – የአካል ብቃት ህክምና /physical therapy/

“እኔ በህክምና ውስብስብነት ወይም ጤናማ ያልሆነ ምግብ በመመገብ የሚከሰት የጤና ችግር የሰውነት አካል ችግር ያለባቸውን ሰዎች መንፈስ ከፍ ማድረግ እፈልጋለሁ፡፡ የአረጋውያን ማእከሎችን በቅርቡ እጎበኛለሁ፤ ከበሽተኞች ጋር በቅርበት እሰራለሁ፤ ሰዎች ቀጣይነት ያለው የስነ-ምግብና አካል ብቃት እንቅስቃሴ የምክር እገዛ ይሻሉ” ትላለች ናኒ፡፡

“የጤናና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ሴቶች ልጆቻችን ጠንካራና ከፍርሀት-ነጻ ሆነው እንዲያድጉ ይረዳቸዋል፡፡” የምትለው ናኒ ባለፉት አስር ዓመታት በኢትዮጵያ በሚገኙ ከተሞች በሴቶች እኩልነትና ሁለንተናዊ አቅም ግንባታ ሂደት ተጨባጭ ለውጥ ተገኝቷል ስትል ትገልጻለች፡፡ ነገር ግን ልክ በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት እንደሚስተዋለው አሁንም መሻሻል የሚገባቸው ነገሮች አሉ፡፡

ሴቶች ከወንዶች በበለጠ መሰረታዊ የሆኑ የኢኮኖሚ ችግሮች አሉባቸው፡፡ በተለምዶ ሴቶች ከሚስትነትና ከእናትነት ያለፈ ሚና እንድትጫወት አይደረግም፡፡ እንደ እድል ሆኖ ናኒ በምትሰማራባቸው ዘርፍ ስኬታማ እንድትሆን ከወላጅ አባቷና ከቤተሰቦቿ ከፍተኛ ድጋፍ አላት፡፡ “የቤተሰቦቼ እገዛና ቅንነት እምቅ ኃይሌን አቀጣጥሎታል” ብላለች ናኒ፡፡

ናኒ እንደምትለው በኢትዮጵያ የሥርዓተ-ጾታ ጉዳዮች ዕይታ ሙሉ በሙሉ አልተለወጠም። ምክንያቱ ደግሞ አሁንም ድረስ በርካታ ሴቶች እራሳቸውን ከወንዱ አሳንሰው ስለሚመለከቱ ነው፡፡ ሴት ልጅ ገና ከሕጻንነት ጀምሮ ሁሉንም እንደምትችል ተደርጋ ማደግ አለባት፡፡ ለበርካታ ዓመታት ወንዶች ልጆች ጠንካራና ደፋር ሆነው እንዲያድጉ የጤናና የአካል ብቃት ልምምድ ወሳኝ ሚና እንደነበረው ሁሉ ሕጻናት ሴት ልጆቻችንም ይህን እድል እንዲያገኙ ማድረግ ይገባል፡፡

በአሁኑ ጊዜ የአካል ብቃት እንቅስቃሴነ የአዕምሮ ጤና የሚፈጥሩት አዎንታዊ ተጽዕኖ በማደግ ላይ መሆኑን መገንዘብ ቀላል ነው፡፡ ለምሳሌ እኔ ከ 1 ሰዓት እስከ 30 ደቂቃ፤ ከ 80 እስከ 100 ኪ.ግ ክብደት፤ ፑሽ አፕ /push-ups/ ቁጭ ብድግ /squats/፣ ወደፊት ወደ ኋላ /pull-ups/ እና የልብ አተነፋፈስ /cardio/ የመሳሰሉ እንቅስቃሴዎችን በማከናወን አነሳለሁ፡፡ ይህ በሰውነት ላይ የሚታይ ጫና ሊፈጥር ይችላል፡፡

ለዚህም ነው እኔ ሀሳብን ከሚሰርቁና ከሚረብሹ ማንኛውም ነገሮች ለማስወገድ የመመሰጥ /meditation/ ልምምድ የማደርገው፡፡ ይህ ደግሞ የውስጥ በራስ መተማመንን ለማጠንከር እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡

በተጨማሪም ናኒ ስለ ኮረና ቫይረስ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራን ስለ አመጋገብና ጤነኛ ህይወት ስለመኖር የተመለከቱ ጉዳዮችን በውይይት መልክ በማንሳት አዘጋጅታለች። በርካታ ጥናቶች እንደሚያመላክቱት በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ስጋት ብዙዎቻችን አብዛኛውን ጊዜያችንን በቤት ውስጥ እንደምንቆይ የታወቀ ነው።

ናኒ በአሁኑ ወቅት ጊዜያቸውን  በቤት ውስጥ በማሳለፍ በሽታውን በመከላከል ጤናማ ህይወት ለመኖር፣ በየቀኑ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መርሀ-ግብር የሚያከናውኑ ሠዎችን የሚያግዝ የመገናኛ ብዙሀን አገልግሎት በመስጠት ላይ ትገኛለች። ናኒ ጤናው ዘውዴ በቃና ቴሌቪዥን የአንድ ለአንድ ቃለ መጠይቅ መርሀ-ግብር ላይ “Stay in- Stay Fit during COVID-19” ጠቀሜታ በተመለከተ ያደረገችውን ቆይታ መለስ ብለው ይከታተሉ። ቤት መቆየት ብቁና ጤነኛ መሆን እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫ በሚያካሂድባቸው ቦታዎች ሁሉ እሳተፋለሁ

በዘንድሮው ሀገራዊ ምርጫ እንደሚሳተፍ ያስታወቀው የኢትዮጵያ ዜጎች ለማሕበራዊ ፍትህ...

በሲዳማ ክልል ከ62% በመቶ በላይ የሚታረሰው መሬት በአሲዳማነት የተጎዳ ነዉ

በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ የሚታየው የምርታማነት ማነቆ በዋናነት የመሬት አሲዳማነት...

የኢትዮጵያ እዳ እና ሃብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን የሥራ ኃላፊዎች ስብሰባ ሳይገኙ ቀሩ

የመንግስት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ እዳ እና...

የኢትዮጵያ እና ሕንድ የቆየ ዲፕሎማሲዊ ግንኙነት

የኢትዮጵያ እና ሕንድ የቆየ ዲፕሎማሲዊ ግንኙነት የአፍሪካ-ሕንድ...