ንብ ባንክ መደበኛ የንግድ ስራ ላይ የሚገኙ ሴቶችን ለመደገፍ እየሰራሁ ነዉ

Date:

ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት በንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዓለም ዓቀፍ ባንክ አገልግሎት ምክትል ኦፊሰር ሐረገወይን አምሳለ፤ ትልልቅ ቢዝነስ ላይ የሚገኙ ሴቶች በአንድም በሌላም መልኩ ተደራሽ ሆነዋል ያሉ ሲሆን፤ አላማችን መደበኛ የቢዝነስ ስራ ላይ ያሉት ጋር መድረስ ነዉ ብለዋል፡፡

ሴት ስራ ፈጣሪዎች ከመነሻ ካፒታል እና ሌሎች የፋይናንስ አገልግሎቶችን ከማግኘት አንጻር የተለያዩ ፈተናዎች እንደሚገጥማቸውም ገልጸዋል፡፡

የሴቶች ተሳታፊነትን ለማጎልበት የተለያዩ የቁጠባ እና የብድር ዘዴዎች ባንኩ ማመቻቸቱን የነገሩን ሲሆን፤ ይህንን እንዲያግዝ ከተባበሩት መንግስታት ሴቶች ጋር ስምምነት መደረጉን አንስተዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ሴቶች የፋይናንስ አካታችነትን የሚከተል በመሆኑ፤ከጉሊት ችርቻሮ ጀምሮ መደበኛ የንግድ ስራ ላይ ለሚገኙ ሴቶች ድጋፎችን እንድናደርግ ያግዘናል ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ያሉ የፋይናንስ ተቋማት ለሴቶች ብድር የሚሰጡት ከ13 በመቶ ባነሰ መጠን ነዉ የተባለ ሲሆን፤ ከወንዶች አንጻር ሲታይ ያነሰ መሆኑ ተገልጿል፡፡

አሁን በስራ ላይ በሚገኙ ባንኮች ላይ በሃላፊነት እየሰሩ ያሉ ሴቶች 12 ነጥብ 5 በመቶ መሆናቸዉ የተገለጸ ሲሆን፤ንብ ባንክ ካሉት ከ7ሺህ በላይ ሰራተኞች 2ሺህ4መቶ20ዎቹ ሴቶች መሆናቸዉን ነግረዉናል፡፡

107.8 f.m

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫ በሚያካሂድባቸው ቦታዎች ሁሉ እሳተፋለሁ

በዘንድሮው ሀገራዊ ምርጫ እንደሚሳተፍ ያስታወቀው የኢትዮጵያ ዜጎች ለማሕበራዊ ፍትህ...

በሲዳማ ክልል ከ62% በመቶ በላይ የሚታረሰው መሬት በአሲዳማነት የተጎዳ ነዉ

በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ የሚታየው የምርታማነት ማነቆ በዋናነት የመሬት አሲዳማነት...

የኢትዮጵያ እዳ እና ሃብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን የሥራ ኃላፊዎች ስብሰባ ሳይገኙ ቀሩ

የመንግስት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ እዳ እና...

የኢትዮጵያ እና ሕንድ የቆየ ዲፕሎማሲዊ ግንኙነት

የኢትዮጵያ እና ሕንድ የቆየ ዲፕሎማሲዊ ግንኙነት የአፍሪካ-ሕንድ...