አምስት ህፃናት በከሰል ጭስ ታፍነው ህይወታቸው አለፈ

Date:

በትግራይ ዓድዋ ከተማ አሉላ ጣቢያ (እንዳ ገብርኤል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ)፣ በታላቁ የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል ላይ፣ ባጋጠመ አሳዛኝ አደጋ የ5 ህፃናት ሕይወት ማለፉ ተገለጸ፡፡

ሕፃናቱ በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ተኝተው ሳለ በከሰል ጭስ (Carbon Monoxide) መታፈን በድንገት ሕይወታቸው ማለፉን የዓድዋ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል፡፡

ከእነዚህም መካከል ሦስቱ የአንድ ቤት ልጆች ሲሆኑ፣ ሁለቱ ደግሞ የአባወራው እህት ልጆች ናቸው ተብሏል።

አሰተዳደሩ ባስተላለፈው የሃዘን መግለጫ፤ “የዓድዋ ከተማ አስተዳደርና መላው የከተማዋ ነዋሪዎች በዚህ ድንገተኛና ልብ የሚሰብር መርዶ የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጹ፤ ለወላጆች፣ ለቤተሰቦችና ለወዳጅ ዘመዶች መጽናናትንና ብርታትን ይመኛሉ። ” ብሏል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አቶ ይህንዓለም አቅናው የአማራ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆኑ

በኢትዮጵያ በፍጥነት እያደጉ ከሚገኙ እና ከፍተኛ የባለአክስዮኖች ቁጥር ካላቸው...

ማዕቀቦች የኢራንን የኒውክሌር መርሃ-ግብር ቢያደናቅፉም መንግስቱን ሊጥሉ እንደማይችሉ ተገለጸ

ማዕቀቦች የኢራንን ወታደራዊ እና የኒውክሌር እንቅስቃሴዎች አስቸጋሪና ውድ እንዲሆኑ...

የአፍሪካ ሀገራት አዲስ የኢንቨስትመንት ፈንድ ይፋ አደረጉ

በአፍሪካ ሀገራት ላይ የተደቀነውን ከፍተኛ የብድር ጫና ለማቃለል እና...

ዶናልድ ትራምፕ “በቅርቡ” ሆርሙዝ የአሜሪካ ግዛት አካል እንደሚሆን ተናገሩ

ከኢራን ጋር ያለው ግጭት እየተባባሰ ባለበት በአሁኑ ሰዓት የአሜሪካው...