አርሶ አደሮች በቀጣይ 10 ቀናት በአጭር ጊዜ የሚደርሱ ሰብሎችን በመዝራት የበልግ ዝናቡን ሊጠቀሙበት ይገባል ተባለ

Date:

በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች እየጣለ ያለውን የበልግ ዝናብ በመጠቀም፤ አርሶ አደሮች በአጭር ወራት የሚደርሱ ሰብሎችን በመዝራት ምርታማነታቸውን ሊያሳድጉ እንደሚገባ ግብርና ሚኒስቴር አሳስቧል።

ሚኒስቴሩ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ አርሶ አደሮች ክረምትን ጨምሮ በሦስት የምርት ወቅቶች ላይ የተሸለ ምርት እንዲያመርቱ እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡ 

የሚንስትሩ የሕዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚ ከበደ ላቀው ለአሐዱ እንደተናገሩት፤ ለበጋ መስኖ እና ለበልግ አምራች ገበሬዎች የቴክኖሎጂ እና የግብዓት አቅርቦት ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል፡፡

ከአቅርቦት ተደራሽነት በተጨማሪም የሥልጠና፣ የውይይት እና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል፡፡

አክለውም ለሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው ግብርናውን ማዘመን ግንባር ቀደም ሚና እንደሚጫወትም ሥራ አስፈጻሚው ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት በበኩሉ፤ ከዛሬ ጀምሮ በሚቀጥሉት አስር ቀናት የበልግ እርጥበት ተጠቃሚ በሆኑት ተፋሰሶች ላይ ከመጠነኛ እስከ ከፍተኛ እርጥበት እንደሚያገኙ አስታውቋል።

ይህም ሁኔታ የገጸ ምድር የውሃ ፍሰትን ስለሚጨምር ወደ ተለያዩ የውኃ ማጠራቀሚያዎች ውስጥ የሚገባውን የውኃ መጠን ከመጨመር አንጻር አዎንታዊ ጎን እንደሚኖረው ገልጿል።

በአንጻሩ ግን ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ላይ ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊያስከትል እንደሚችልም ኢንስቲትዩቱ ባወጣው መረጃ አመላክቷል።

ስለሆነም የጎርፍ ተጋላጭ በሆኑት አካባቢዎች ላይ የጎርፍ ፍሳሽ ማፈሰሻ ቦዮችን በማፅዳት ሊከሰት የሚችልውን ተጽዕኖ ለመከላከል ከወዲሁ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን ማከናወን እንደሚያስፈልግ ገልጿል፡፡
@አሐዱ

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/aha

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አቶ ይህንዓለም አቅናው የአማራ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆኑ

በኢትዮጵያ በፍጥነት እያደጉ ከሚገኙ እና ከፍተኛ የባለአክስዮኖች ቁጥር ካላቸው...

ማዕቀቦች የኢራንን የኒውክሌር መርሃ-ግብር ቢያደናቅፉም መንግስቱን ሊጥሉ እንደማይችሉ ተገለጸ

ማዕቀቦች የኢራንን ወታደራዊ እና የኒውክሌር እንቅስቃሴዎች አስቸጋሪና ውድ እንዲሆኑ...

የአፍሪካ ሀገራት አዲስ የኢንቨስትመንት ፈንድ ይፋ አደረጉ

በአፍሪካ ሀገራት ላይ የተደቀነውን ከፍተኛ የብድር ጫና ለማቃለል እና...

ዶናልድ ትራምፕ “በቅርቡ” ሆርሙዝ የአሜሪካ ግዛት አካል እንደሚሆን ተናገሩ

ከኢራን ጋር ያለው ግጭት እየተባባሰ ባለበት በአሁኑ ሰዓት የአሜሪካው...