አቶ ታዬ ደንደአ አዲስ ሦስት ክሶች ቀረቡባቸው

Date:

የቀድሞ የሰላም ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንደአ ላይ ዐቃቤ ሕግ አዲስ ሦስት አይነት ክሶችን እንዳቀረበባቸው ጠበቃቸው አበራ ንጉስ ተናግረዋል።

አቶ ታዬ በዛሬው ዕለት የቅጣት አስተያየት ለማቅረብ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት የጸረ ሽብር ችሎት ቀርበው፤ ቀድሞ በተሰጣቸው ተለዋጭ ትዕዛዝ መሰረት ጥፋተኛ በተባሉት “የፀና ፍቃድ ሳይኖር የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት” ወንጀል የቅጣት ላይ አስተያየታቸውን ያቀረቡ መሆኑን አብራርተዋል።

በዚህም ዐቃቤ ሕግ የአቶ ታዬ ደንደአ የቀጣት አስተያየት የተቀበለ ሲሆን፤ ችሎቱም የግራ ቀኙ የቅጣት አስተያየት በመመርመር ቅጣት ለመወሰን ለሕዳር 23 ቀን 2018 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በዛሬው የችሎት ውሎ ዐቃቤ ሕግ አዲስ የወንጀል ክስ የከፈተ ሲሆን፤ ይህን አዲስ የወንጀል ፋይል ለአቶ ታዬ ደንደአ በፅሑፍ የደረሳቸው መሆኑን እና በተጨማሪም ችሎቱ በንባብ አስምቷቸዋል ሲሉ ጠበቃው ተናግረዋል።

ዛሬ የቀረበው አዲስ የወንጀል ክስ በይዘት ደረጃ አቶ ታዬ Horn conversation ከተሰኘው የዩቲዩብ ቻናል ጋር ያደረጉት እና በሦስት ተከታታይ ምዕራፍ ከቀረበው ፕሮግራም ጋር የተያያዘ ሲሆን፤ በክሱ ሦስት ተደራራቢ ወንጀሎች ቀርቦውባቸዋል ሲሉ ጠበቃቸው አቶ አበራ ንጉስ አብራርተዋል።

የመጀመሪያው ክስ የወንጀል ሕግ ቁጥር 257(ሀ)፡ (ሰ) በመጥቀስ የቀረበ ሲሆን፤ የወንጀል መጠሪያውም “መንግሥትን በኃይል ለመጣል ግዙፋዊ መሰናዶ ማድረግ” ሲሆን፣ ሁለተኛው ክስ ደግሞ የወንጀል ሕግ አንቀፅ 337 በመጥቀስ የቀረበ “የሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ ሃሰተኛ እና አደናጋሪ ወሬዎችን መንዛት የሚል ነው ብለዋል።

በስተመጨረሻ የቀረበባቸው ክስ የወንጀል ህግ አንቀፅ 244(1) በመጥቀስ፤ “በሕገ-መንግሥት መሰረት የተመረጠ የሀገሪቱ መንግሥት መድፈር” የሚል መሆኑን ከዛሬው የችሎት ውሎ መረዳት መቻላቸውን  ጠበቃው ገልጸዋል።

አቶ ታዬ ደንደአ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ጸረ ሽብር ችሎት “ከጠላት ጋር መተባበር”፣ መገፋፋትና ግዙፋዊ መሰናዳት እንዲሁም፤ የፀና ፍቃድ ሳይኖር የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት በሚል ሦስት ተደራራቢ ወንጀሎች ተከሰው በክርክር ሂደት ላይ እንደነበሩ የሚታወስ ሲሆን፤ ፍርድ ቤቱ ሕዳር 3 ቀን 2018 ዓ.ም. ባስተላለፈው ውሳኔ ‘ተከሳሹ ከተጠረጠሩበት ሦስት ወንጀሎች በሁለቱ ነጻ ናቸው’ ማለቱ አይዘነጋም።

ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ አቶ ታዬ ጥፋተኛ በተባሉት አንድ ክስ ማለትም “የፀና ፍቃድ ሳይኖር የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት” ክስ የቅጣት አስተያየት ለመስማት ለዛሬ ሕዳር 15 ቀን 2018 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶ የበነረ ሲሆን፤ በዛሬው የችሎት ውሎውም የቀጣት አስተያየቱን በመቀበል ቅጣት ለመወሰን ለሕዳር 23 ቀን 2018 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

(አሐዱ ሬዲዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...

የኢትዮጵያ አጠቃላይ ብድር 51.8 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ይፋ ሆኗል

ኢትዮጵያ  በድጋፍ መልክ ከአሜሪካ በየዓመቱ  በመንግስት በኩል ፈሰስ የሚደረግ...

ከ8 ሺህ በላይ ጥንታዊ የብራና ጽሑፎችን እና ሰነዶችን ወደ ዲጂታል ተቀየሩ

የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብት እና ቤተ መጽሐፍት አገልግሎት ከተለያዩ ተቋማት፣...

አቶ ዳውድ ኢብሳ ከምርጫው ራሳቸውን አገለሉ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ በኦሮሚያ...