አዋሽ ባንክ በግሎባል ፋይናንስ ለ4ኛ ጊዜ የአፍሪካ ምርጥ ባንክ ተባለ

Date:


አዋሽ ባንክ ለ4ተኛ ጊዜ ከ36 ምርጥ የአፍሪካ ባንኮች ውስጥ በመካተት ከኢትዮጵያ ብቸኛ ምርጥ ባንክ በመባል ተመረጠ።

ግሎባል ፋይናንስ እ.ኤ.አ. በማርች 2025 ለ32ኛ ጊዜ እ.ኤ.አ. ለ2025 የምርጥ ባንኮችን ምርጫን ይፋ ማድረጉን አስመልክቶ አዋሽ ባንክ ዛሬ መጋቢት 25/2017 ዓም በዋና መስሪያ ቤቱ በሰጠው መግለጫ ከአፍሪካ ዉስጥ ምርጥ ባንኮች ተብለዉ ከተመረጡ 36 ባንኮች መካከል አዋሽ ባንክ በተከታታይ ለ4ኛ ጊዜ መመረጡንና ከኢትዮጵያ ደግሞ ብቸኛ ባንክ መሆኑን ይፋ አድርጓል፡፡

አዋሽ ባንክ ከ36 ምርጥ የአፍሪካ ባንኮች ውስጥ የተመረጠ እንደሆነ የተነገረ ሲሆን ከኢትዮጵያ ደግሞ ብቸኛው ምርጥ ባንክ ተብሎ ሊመረጥ የቻለውም በግሎባል ፋይናንስ ሜጋዚን የምርጫ መስፈረቶች መሰረት ባንኩ እ.ኤ.አ. በ2024 ባከናወነው የኦፐሬሽን እና ኦፕሬሽን ነክ ባልሆኑ ሥራዎች መሆኑ ታውቋል ተገልጿል።

በድርጅቱ የዕድገት መለኪያዎች ባንኩ ከምርጥ ባንኮች አንዱ ሆኖ ሊመረጥ በየቻለው ቁልፍ በሆኑ የፋናንስ የዕድገት መለኪያዎች ማለትም በጠቅላላ ሃብት ዕድገትና በሀብት መጠን፣ በአጠቃላይ ዓመታዊ ገቢ ዕድገትና ዓመታዊ ትርፍ፣ በብድር አቅርቦት፣ በተከፈለ ካፒታል ዕድገትና በትርፍ ድርሻ ክፍፍል መሆኑ ተነግሯል።

በሌላ በኩል ፋይናንስ ነክ ባልሆኑ የእድገት መለኪያዎች ማለትም በደንበኛ ብዛትና በገበያ ድርሻ ዕድገት፣ ጥልቀት በብራንድ ግንባታ፣በቅርንጫፎች ስርጭት ረገድ ተደራሽነቱን በማስፋቱ፣ ዘመኑን በዋጁ አዳዲስ የባንክ ፕሮዳክቶችንና አገልግሎቶችን በማስፋፋቱና ለህብረተሰቡ ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠቱ፣ እንዲሁም አስፈላጊ የሆኑ የክፍያ አገልግሎቶችን በማስፋፋቱ ሲሆን በተጨማሪም የተለያዩ ታዋቂ የፋይናንስ ዘርፍ ተንታኞች እና ሌሎች የዘርፉ ባለሙያዎች የሰጡት ድምፅ ታሳቢ ተደርጎ ከኢትዮጵያ ብቸኛው ምርጥ ባንክ ሆኖ ለአራተኛ ጊዜ መመረጥ እንደተቻለ ተገልጿል።

አዋሽ ባንክ በኦክቶበር ወር በአሜሪካ በሚዘጋጅ ፕሮግራም ሽልማቱን እንደሚቀበል ተገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግብጻዊቷ የቴሌቪዥን አዘጋጅ በዕፅ ዝውውር ወንጀል የሞት ፍርድ ተወሰነባት

የካይሮ የወንጀል ችሎት፤ ዕውቋን የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ ሳራ ካሊፋን...

ከአሜሪካ ጋር የሚኖረው “የጨዋታው ሕግ ተቀይሯል፤ የተመጣጠነ ምላሽ ዘመን አብቅቷል

ኢራን ከአሜሪካ በኩል ለሚሰነዘርባት ጥቃት የምትሰጠው ተመጣጣኝ የአጸፋ ምላሽ...

የ2.5 ቢሊየን ብር ግዙፍ ፕሮጀክት በአታ ለማርያም ገዳም በመስከረም ወር የመሠረት ድንጋይ ሊያኖር ነዉ

​በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ የታዕካ ነገሥት...

የዲቪ ዕድለኞች የማመልከቻ ሂደታቸውን እንዲቀጥሉ ተወሰነ!

የአሜሪካ የፌዴራል ፍርድ ቤት በዲቪ ሎተሪ አመልካቾች የማመልከቻ ሂደት...