የምስሉ መግለጫ,አያቶላህ አሊ ኻሜኒ
የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ ለኢራን ሕዝብ “ጠላት እንደምትፈሩት ከተሰማው አይለቃችሁም” ሲሉ ሕዝባቸው በጥንካሬው እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።
መሪው በኤክስ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት ሕዝባቸውን “እስከ ዛሬ ድረስ በነበራችሁ ባህርይ ቀጥሉ፣ ይህንንም ባህርያችሁን በጥንካሬ በመያዝ ጸንታችሁ ቀጥሉ” ብለዋል።
ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ለአርብ አጥቢያ እስራኤል ኢራን ውስጥ የፈጸመችው ጥቃት ተከትሎ ሁለቱ አገራት አንዳቸው በሌላኛቸው ላይ አውዳሚ ጥቃት መፈጸማቸውን ቀጥለዋል።
በእስካሁኑ ጥቃት የኒውክሌር ማዕከላት፣ ወታደራዊ እና የመንግሥት ተቋማት፣ የመገናኛ ብዙኃን፣ የሰላማዊ ሰዎች መኖሪያ እና ተቋማት ጉዳት ደርሶባቸዋል። በሁለቱም ወገን በመቶቹ የሚቆጠሩ ሰዎች መገደላቸውን እና ሺዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው እየተነገረ ነው።
