አዲሱ የኢራን ጠቅላይ መሪ ጉዳት ደርሶባቸው ከጥቃት መትረፋቸው ተነገረ

Date:

የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ መሪ ሆነው የተመረጡት የቀድሞው መሪ ልጅ ሞጅታባ ኻሜኒ ያሉበት የጤናን ሁኔታ በተመለከተ የሚወጡ መረጃዎች አሳሳቢ እየሆኑ መምጣታቸውን ዘገባዎች እያመለከቱ ነው።

የአዲሱ ጠቅላይ መሪ ደኅንነት እንዲሁም ከተመረጡ በኋላ ለሕዝብ በይፋ አለመታየታቸው አጠያያቂ ከመሆኑ በተጨማሪ ለኢራን መንግሥት ቅርበት ያላቸው ምንጮች የሚሰጧቸው መረጃዎች የሞጅታባ ጤንነት ላይ ጥያቄ ፈጥሯል።

በቆፕሮስ የኢራን አምባሳደር የሆኑት አሊሬዛ ሳላሪያን ለብሪታኒያው ጋዜጣ ‘ዘ ጋርዲያን’ ጠቅላይ መሪው “እግር እና እጆቻቸው ላይ ጉዳት እንደደረሰባቸው ሰምቻለሁ… የመቁሰል ጉዳት ስለደረሰባቸው ሆስፒታል እንደሆኑ አስባለሁ” ሲሉ ተናግረዋል።

የሞጅታባ ደኅንነት ጉዳይ አነጋጋሪ መሆኑን ተከትሎ የፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን በቴሌግራም ገጹ ላይ ጠቅላይ መሪው ጉዳት እንደደረሰባቸው የሚገልጹ “ሪፖርቶችን አይቻለሁ” በማለት፣ ነገር ግን ሞጅታባ ደኅና መሆናቸውን ማረጋገጡን ጽፏል።

በተጨማሪም ሰኞ ዕለት የሞጅታባ መመረጥ ዜና ከወጣ በኋላ የኢራን መንግሥት ቴሌቪዥን ጉዳት ደርሶባቸው እንደነበር ቢጠቅስም ምንም ዓይነት ዝርዝር ግን ሳይሰጥ ቀርቷል።

ቆፕሮስ ያሉት የኢራን አምባሳደር ጨምረው እንዳብራሩት ሞጅታባ ኻሜኒ ጉዳት የደረሰባቸው አባታቸውን እና ሌሎች አምስት የቤተሰባቸው አባላት በተገደሉበት ጥቃት መሆኑን አመልክተዋል።

ሞጅታባ የኢራን ጠቅላይ መሪ ሆነው ከተሰየሙ ሦስት ቀናት ያለፏቸው ቢሆንም እስካሁን ከእሳቸው በኩል ምንም ዓይነት መልዕክትም አልተሰማም፤ በአደባባይ አልታዩም ወይም ንግግር አላደረጉም ።

አምባሳደሩ ይህንን በተመለከተ ለ ዘ ጋርዲያን እንደተናገሩት “በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ንግግር ለማድረግ የሚፈልጉ አይመስለኝም” ብለዋል።

በመጀመሪያው ቀን የአሜሪካ እና እስራኤል ጥቃት የተገደሉ ወታደራዊ አዛዦች የቀብር ሥነ ሥርዓት በዛሬው ዕለት የተፈጸመ ሲሆን፣ ነገር ግን ጠቅላይ መሪው ሞጅታባ ኻሜኒ አልተገኙም።

በቆጵሮስ የኢራን አምባሳደር ለጋዜጣው ሟቹ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ በሕይወት እያሉ የሃይማኖት መሪዎች ልጃቸው እንዲተካቸው ጥያቄ ቢቀርብላቸውም የቤተሰብ ሥርዓት እንዲሆን እንደማይፈልጉ በመግለጽ መቃወማቸውን ተናገረዋል።

ነገር ግን ከአባታቸው መገደል በኋላ የከፍተኛ ሊቃውንቱ ጉባኤ ሞጅታባን ለመሪነት በመሰየም “ኃላፊነቱ የአንተ ነው መቀበል አለብህ” በማለት ለመሪነት እንደመረጧቸው ገልጸዋል።

የአያቶላህ ኻሜኒ ግድያን በተመለከተም መኖሪያ ቤታቸው ከፕሬዝዳንታዊው ቤተ መንግሥት አቅራቢያ ስለነበረ ጥቃቱ ሲፈጸም ሚስታቸው፣ ሴት ልጃቸው፣ ባሏ እና የ14 ዓመት ልጇ ጭምር መገደላቸውን አረጋግጠዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...