ኢራን በዛሬው ዕለት በፈጸመቻቸው የሚሳኤል ጥቃቶች የተጎዱ ሰዎች ቁጥር ወደ 89 ከፍ ማለቱን የእስራኤል የድንገተኛ አደጋ አገልግሎት ማጌን ዴቪድ አዶም አስታወቀ።
በተጨማሪ በቴልአቪቭ እና በደቡብ የሃገሪቱ ክፍል የተወነጨፉ ሮኬቶች ሶስት ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት ማድረሳቸውን እንዲሁም ሁለቱ ደግሞ በመካከለኛ ሁኔታ ላይ ናቸው ብሏል።
አብዛኛዎቹ የተጎዱት በፍንዳታዎች እንዲሁም በስብርባሪ እና ፍንጣሪዎች መሆኑን የህክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ።
በእስራኤል ደቡባዊ ክፍል ቤርሼባ በተሰኘች ከተማ የሚገኝ ሆስፒታል በኢራን የሚሳኤል ጥቃት ተመትቷል።
ኢራን የሚሳኤል ጥቃቱ ኢላማ በሆስፒታሉ አቅራቢያ የሚገኝ ወታደራዊ ይዞታ መሆኑን አስታውቃለች።
BBC Amharic
