ዋልያ አይቤክስን የሚገድሉ አካላት በሐይማኖት አባቶች እንዲወገዙ ተደርጓል

Date:

የመጥፋት አደጋ ያጋጠመው ብርቅዬው ዋልያ አይቤክስ ቁጥር ወደ 306 መውረዱንና የህልውና አደጋውን ለመቀነስ ዋልያ የሚገድሉ አካላት በሐይማኖት አባቶች እንዲወገዙ መደረጉን የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን አስታወቀ።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኩመራ ዋቅጅራ ቀደም ባሉት ጊዜያት ዋልያ እንደማይታደን እና ስጋው እንዳይበላ በሐይማኖትም ተወግዞ የቆየ መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህ ተግባር ከተወሰነ ዓመት ወዲህ እየተሸረሸረ መጥቶ ድምጽ አልባ በሆነ መንገድ እየታደነ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

በዚህም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ብቻ የሚገኘው ዋልያ አይቤክስ በከፍተኛ መጠን የመጥፋት አደጋ እንዳጋጠመው እና በቁጥርም ወደ 306 መውረዱን አስታውቀዋል።

የዋልያ አይቤክስ ቁጥር እንዲያገግም በጋራ መስራት እንደሚያስፈልግ ለኢፕድ የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፤ በዚህም ብሔራዊ የጥበቃ ስትራቴጂ አዘጋጅቶ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ከአንድ ወር በፊት ወደስራ መግባቱን ገልጸዋል።

የ #ኢትዮጵያ ብቻ መገለጫ የሆነ ብርቅዬ ሀብት ከምድራችን እንዳይጠፋ ለማድረግና ህልውናውን ለመታደግ እንዲሁም ለመጠበቅ ከ #ደባርቅ_ዩኒቨርሲቲ ጋር በቅንጅት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

ህገ ወጥ እንቅስቃሴን ለመቆጣጠር እና የብርቅዬ እንስሳቱን ቁጥር ተመልሶ እንዲያገግም ለማድረግ “የዋልያ አምባሳደር” የተሰኘ ስያሜ የተሰጣቸው የአካባቢው ማህበረሰብ አካላትን በማደራጀት የ24 ሰዓታት የቁጥጥር ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በተጨማሪም የስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ አቅምን ለማሳደግ የተሽከርካሪ፣ የፋይናስ፣ የስልጠና ድጋፍ እንዲሁም የሬንጀሮችን ብዛት የመጨመር ስራ መሰራቱን ተናግረዋል።

ዋልያ አይቤክስ በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ የሚገኝ ብርቅዬ የዱር እንስሳት መሆኑ የተረጋገጠው በ1953 ዓ.ም ሲሆን፤ በ #ዩኔስኮ የዓለም ቅርስነትም ተመዝግቧል።
Addis standard

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 1 2018 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

በኢትዮጵያ ነፃ ኘሬስ ከ25 ዓመት በላይአገልግለናል !!! -የአርበኞች አደራና የትውልዱ...

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...

በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ  የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ለዓለም የንግድ ሰንሰለት እጅግ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ባህረ ወሽመጥ...

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...